top of page

መስከረም 21፣2017 - የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የአለም አቀፍ የደረጃዎች ድርጅት መስፈርቶችን በማሟላቱ የISO 9001፣ 2015 የምስክር ወረቀት ማግኘቱን ተናገረ

  • sheger1021fm
  • Oct 1, 2024
  • 1 min read

የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የአለም አቀፍ የደረጃዎች ድርጅት መስፈርቶችን በማሟላቱ የISO 9001፣ 2015 የምስክር ወረቀት ማግኘቱን ተናገረ፡፡


በዚህም የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያው የመንግስት ዩኒቨርሲቲ ለመሆን መብቃቱን ሰምተናል፡፡


የምስክር ወረቀቱ ዩኒቨርሲቲው በትምህርት፣ በምርመራ እና በአገልግሎት አሰጣጥ የላቀ ደረጃን ለማረጋገጥ ለሚያደርገው ስራ ብርቱ አጋዥ እንደሚሆነው ተናግሯል፡፡


የዩኒቨርስቲው የአካዳሚ ጉዳዮች ም/ፕሬዘዳንት ከማል ኢብራሂም(ዶ/ር) ዩኒቨርስቲው የአለም አቀፍ ደረጃ ድርጅት (ISO) የምስክር ወረቀት ለማግኘት ሰፊ የአሰራር ሥርዓቶችን ማስተካከልን ጠይቆታል ብለዋል፡፡


ዩኒቨርስቲው የISO የምስከር ወረቀትን ከነገ በስቲያ እንደሚቀበል ሰምተናል፡፡


ለዩኒቨርስቲው የተሰጠው የምስክር ወረቀት ለመጪዎቹ 3 ዓመታት እንደሚያገለግል ዶ/ር ከማል ነግረውናል፡፡


የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ለመጀመሪያ ዲግሪ በ13 ፕሮግራሞች፣ ለሁለተኛ እና ሶስተኛ ድግሪ በ40 ፕሮግራሞች ተማሪዎችን እያስተማረ እንደሆነ ሰምተናል፡፡


ዩኒቨርሲቲው በዘንድሮው የትምህርት ዘመን ከ6,000 በላይ ተማሪዎች እንደሚያስተምር አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዘዳንቱ ለሸገር ኤፍ ኤም ራዲዮ ተናግረዋል፡፡



ንጋቱ ሙሉ

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page