አቤቱታ እንዲቀበል፣ እንዲያጣራ እና የውሳኔ ሃሳቦችን እንዲያቀርብ በአዋጅ የተቋቋመው የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም፤ የሚያቀርባቸውን ምክረ ሃሳቦች የማይቀበሉ ብሎም የማይፈጽሙ የስራ ሃላፊዎች መኖራቸውን በተደጋጋሚ ሲናገር ቆይቷል፡፡
በኦሮሚያ፣ በአማራ እና በትግራይ ክልሎች ያሉ የተቋሙ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች የሚሰጧቸውን ምክር ሃሳቦች ለመፈጸም ፍቃደኛ የማይሆኑ የስራ ሃላፊዎች መኖራቸውን ተናግረዋል፡፡
የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ከማቀርባቸው ምክረ ሃሳቦች የሚፈጸሙት 60 በመቶቹ ናቸው ብሏል፡፡
ተቋሙ ይህም የሚያሳየው ከፍተኛው የስልጣን አካል የሆነው የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ላወጣው ህግ አለመገዛትን ነው ብሏል፡፡
አንዳንዶች ድግሞ የፍርድ ቤትን ትዕዛዝ ጭምር አልቀበልም የሚሉ አሉ ተብሏል፡፡
ለመሆኑ የሚፈጸሙ አስተዳደራዊ በደሎች መፍትሄ አለማግኝት በመንግስት እና በህዝብ መካከል የሚያሳድረው ተጽዕኖ ምንድነው?
በጉዳይው ላይ የህግ ባለሞያን ጠይቀናል፡፡
ያሬድ እንዳሻው
Comments