ዋሽንግተን ይህንን ያለችው የአሜሪካ መንግስት የልማት ተራድኦ ድርጅት ዩኤስአይዲ(USAID) በአውሮፓዊያኑ 2020 የጀመረውን አለመግባባቶች በውይይት እንዲፈቱ ታሳቢ ያደረገ የ5 ዓመት ፕሮግራሙን ማጠናቀቁን ይፋ ባደረገበት ወቅት ነው፡፡
በዚህም ወቅት በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ምን አሉ?
‘’ለዓመታት የዘለቀ ግጭት ባለባቸው የአማራ፣ የትግራይና የኦሮሚያ ክልሎች ማህበረሰቡ ላይ በማተኮር ሲሰራ የቆየው የኢትዮጵያ ድጋፍ ፕሮግራም ብዙ ውጤት አስገኝቷል፡፡
በኢትዮጵያ ተባብሰው የቀጠሉት ግጭቶች በማህበረሰቡ ላይ እንዲሁም በኢኮኖሚው ላይ የተወሳሰቡ ችግሮችን ማስከተላቸውን የጠቀሱት አምባሳደሩ፣ ለአብነትም ኢትዮጵያ ከጦርነቱ በፊት ለተከታታይ 10 ዓመታት ከ8 እስከ 10 በመቶ የኢኮኖሚ እድገት ታስመዘግብ ነበረች ቢሆንም በከአስርቸ ዓመታት በፊት ከነበረበት በአሁኑ ወቅት እድገቷ በ2.5 በመቶ አሽቆልቁሏል፡፡
በመሆኑም ችግሮች ከዚህ በላይ ከመክፋታቸው በፊት ግጭት ውስጥ ያሉ አካላት ወደ ውይይት እንዲመጡ ጥሪ እናቀርባለን፤ በዚህም አሜሪካ የወትሮ ድጋፏል ታደርጋለች፡፡’’
በተጨማሪ የኢትዮጵያ ድጋፍ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ተወካይ ሳም ሳገር ፕሮጀክቱ ምን ውጤት አመጣ ላልናቸው ይህንን ብለዋል፡፡
‘’ባለፉት 5 ዓመታት በተከወነው ‹‹የኢትዮጵያ ድጋፍ ፕሮግራም‹‹በተሰኘው የዩኤስ አይዲ ፕሮግራም ድርጅቱ 189 ከሚደርሱ የሀገር በቀል ድርጅቶች ጋር በመሆን ድጋፍ የተደረገባቸው 375 አይነት ስራዎች ተከውነዋል፣
በግጭት አካባቢዎች የመልሶ ግንባታ ተከውኗል፣ ለተጎጂዎች የስነ ልቦና ድጋፍ ተደርጓል፤ እነዚህ ፕሮግራሞች በግጭቶች ምክንያት የተከፋፈሉ የማህበረሰብ ክፍሎችን ለማቀራረብ፤ አንገብጋቢ በሆኑ የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ሰፋፊ ውይይቶች እንዲደረዱ ረድተዋል፤
ፕሮግራሙ በተለያየ መንገድ ከእኛ ጋር ሲሰሩ የነበሩ አጋሮቻችንን በአንድ ላይ ያሰባሰበ ነው፤ምንም እንኳን ይህ የ5ዓመት ፕሮግራም ቢያበቃም ዩ ኤስ አይዲ በኢትዮጵያ የሚከውናቸው ዘርፈ ብዙ ስራዎች አሉት፤ በስራዎቹ ይገፋበታል፡፡’’
የፕሮግራሙ አንድ አካል የሆነውና ባለፈው ዓመት የጦርነቱ ቀጠና ላይ የነበሩ ሰዎች ከደረሰባቸው የስነ ልቦና ቁስለት ለማከም በተሰራው ስራ ተዘዋውረው ይህንን ሲሰሩ የነበሩት ስነ ልቦና ባለሙያዋ ትዕግስት ዋልተንጉስ ለሸገር ራዲዮ እንዳሉት፤
‘’ጦርነት ሲከተት ብዙዎች ትኩረታቸው ለሰዎች ምግብና መጠጥ ማቅረብ ላይ ነው፣በዚህ ውስጥ የሚያልፉ ሰዎች አእምሯቸው በብዙ ተጎድቷል ግን የሚጠይቃቸው እንኳን የለም’’
ባለሙያዋ ‘’በተቻለ መጠን ተጎጂዎችን በመፍረስ ትንሽም ቢሆን ፋታ እንዲያገኙ ምክንያት ሆነናል’’ ይላሉ፡፡
ዩኤስአይዲ በተከወኑት በእነዚህ ስራዎች በተለይ በአማራ እና በትግራ ክልል ያሉ ከ1 ሚሊዮን 76 ሺህ በላይ ሰዎች የተለያየ አይነት ድጋፍ ተደርጎላቸዋል መባሉን ሰምተናል፡፡
ምንታምር ፀጋው
Comments