top of page

መስከረም 20፣2017 - ኢትዮጵያ ህዝቧ በልምድ ያገኙትን እውቀት፤ እውቅና የምትሰጥበትን መምሪያ ይፋ አደረገች

ኢትዮጵያ ህዝቧ በልምድ ያገኙትን እውቀት፤ እውቅና የምትሰጥበትን መምሪያ ይፋ አደረገች፡፡


መመሪያው ከመደበኛ ትምህርት ውጪ በልምድ የሚገኙ እውቀትን ህጋዊ እውቅና እንዲያገኙ የሚያደርግ መሆኑ የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል አስረድተዋል፡፡


መመሪያው ከቤተሰብም ሆነ ከአካባቢ በልምድ የሚገኙ እውቀትን ክህሎሎት እውቅና እንዲኖራቸው ያስችላል ተብሏል፡፡


ይህ መመሪያ ዜጎች በልምድ ያገኙትን እውቀት እውቅና እንዲኖረው የመደራደር አቅማቸው እንዲጨምር፣ በራስ የመተማመን አቅማቸውን እንዲያድግ ይረዳቸዋል ተብሎ ተስፋ ተደርጎበታል፡፡

ከመደበኛው ትምህርት ውጪ የሚገኙ ልምዶችን እውቅና መስጠት ወደ ሀገር የሚገባውን ኢኮኖሚ ያሳድጋልም ሲባል ሰምተናል፡፡


ስራዎችም ጥራታቸውን ጠብቀው እንዲሰሩ ያግዛል ተብሏል፡፡


ኢትዮጵያዊያን ከእናት ከአባቶቻቸው መደበኛ ባልሆነ መንገድ ያገኙትን እውቀት ጥቅም ላይ እንዲያውሉት መመሪያው ይረዳል ሲሉ ሚኒስትሯ ሙፈሪያ ካሚል ተናግረዋል፡፡


ይህ መመሪያ ኢንዱስትሪዎችን፣ ተቋማትን ወይም ግለሰቦችን ብቻ ሳይሆን የሚጠቅመው ወደ ኢኮኖሚው የሚመጣውን ክህሎት ተወዳዳሪ እና ብቁ እንዲሆንም ጭምር ነው ተብሏል፡፡


ሰዎች በየትኛውም የሞያ መስክ በልምድ ያገኙትን እውቀት ህጋዊ ለማድረግ ወይም ህውቅና እንዲኖረው ለማስቻል በየትኛውም የCOC ወይም የብቃት መመዘኛ ተቋማት ሄደው መመዘን ብቻ ይጠበቅባቸዋል ሲባል ሰምተናል፡፡


መመሪያውን የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ሀላፊዎች፣ አለም አቀፍ የስራ ድርጅት(ILO) እና የጀርመኑ ተራድኦ ድርጅት(GIZ) በጋራ በመሆን ይፋ አድርገውታል፡፡


ያሬድ እንዳሻው

Opmerkingen


bottom of page