top of page

መስከረም 2፣2017 - በጉለሌ ክፍለ ከተማ ፅዮን ሆቴል አካባቢ በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ፤ አፋፍ ስር የነበሩ ቤቶች ላይ ጉዳት አድርሷል

  • sheger1021fm
  • Sep 12, 2024
  • 1 min read

ጳጉሜ 4፣2016 በጉለሌ ክፍለ ከተማ ፅዮን ሆቴል አካባቢ በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ፤ አፋፍ ስር የነበሩ ቤቶች ላይ ጉዳት አድርሷል፡፡


የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሞያው አቶ ንጋቱ ማሞ ''በሰው ይህወት ላይ የደረሰ ምንም አይነት ጉዳት የለም ነገር ግን በአደጋው በስፍራው ያሉ 5 ቤቶችን ከጥቅም ውጭ ሆነዋል'' ብለውናል፡፡


ቤቶቹ ውስጥ የነበሩ 24 ሰዎች ጉዳት ሳይደርስባቸው በማውጣት ወደ ሌላ ስፍራ እንደተዛወሩና የአደጋው ምክንያት እተጣራ መሆኑን አቶ ንጋቱ ጠቁመዋል፡፡  


በተጨማሪም የ2017 ዓ.ም አዲስ ዓመትን ተከትሎ ሊከሰቱ የሚችሉ አደጋዎችን ለመከላከል በቂ ዝግጅት ማድረጉን የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ተናግሯል፡፡


በበዓላት ወቅት በአንድ በኩል ለበዓሉ ማድመቂያ የሚሆኑ ግብዓቶችን ግብይት ለመከወን እንቅስቃሴዎች ስለሚኖሩ፤ በሌላ በኩል በቤት ውስጥ የምግብና መጠጦች ዝግጅት ስለሚኖር በአብዛኛው የእሳትና የትራፊክ አደጋዎች እንደሚከሰቱ የጠቆመው ኮሚሽኑ አደጋዎች እንዳይኖሩ መጠንቀቅ እንደሚያስፈልግ ተናግሯል፡፡

ከአቅም በላይ በሆነ ምክንት እንዲሁም በአጋጣሚ አደጋዎች ቢከሰቱ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ኮሚሽኑ በ11ዱም ቅርንጫፎቹ የአደጋ ምላሽ ባለሞዎችና ማሽነሪዎች መዘጋጀታቸውን የህዝብ ግንኙነት ባለሞያው አቶ ንጋቱ ማሞ ነግረውናል፡፡


ከአዲስ ዓመት በኋላም የመስከረም ወር በዓላት ተከታትለው የሚመጡበት በመሆኑ አክባሪዎች በሙሉ በዓሉን ለማክበር ባለው ጥድፊያ ከሚፈጠሩ ስህተቶች ሊጠነቀቅ እንደሚገባና በተለይም በምሽት የመፈጠሩ የእሳት እና በከሰል የመታፈን አደጋዎችን ለመቆጣጠር አዳጋች ስለሚሆን የተለየ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚያስፈል አቶ ንጋቱ ጠቁመዋል፡፡


በዓሉን ተከትሎም ይሁን በማንኛውም ሰዓት ለሚያጋጥሙ ማናቸውም አደጋዎች በ939 ደውላችሁ አሳውቁን ተብላችዋል፡፡


ምንታምር ፀጋዉ

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page