top of page

መስከረም 2፣2016 -ቄራዎች እንሳስትን እያረቡ ስጋውን የሚያቀርቡበት አሰራር ሊኖር ይገባል እየተባለ ነው


በኢትዮጵያ የሚገኙ ቄራዎች ወደ ውጪ ለሚልኩት ስጋ የሚሆኑ የዕርድ እንስሳትን የሚያገኙት ከአርብቶ አደሩ እና አርሶ አደሩ ነው።


በዚህ መልክ የሚገኙ እንስሳት ስጋ በተለይ በውጭ ገዥዎች ተመራጭ እንዳልሆነ ግን ይነገራል።


የውጭ ገዥዎች ፍላጎት ዕድሜያቸው ያልገፋ፤ ስጋቸውም ለጥርስ ያልጠነከረ እንስሳት ስጋ እንደሆነ ይጠቀሳል።


ይህን የገዥዎች ፍላጎት ለማሟላት ቄራዎች በእራሳቸው እንሳስትን እያረቡ ስጋውን ለገዝዎች የሚያቀርቡበት አሰራር ሊኖር ይገባል እየተባለ ነው።


ንጋቱ ረጋሣ



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz

bottom of page