top of page

መስከረም 18፣2016-በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያምና የመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የበላይ ጠባቂ



በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያምና የመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የበላይ ጠባቂ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሰላማ ከዚህ ዓለም አረፉ፡፡


ብፁዕ አቡነ ሰላማ ባደረባቸው ህመም ምክንያት በአዲስ አበባ ሀሌሉያ ሆስፒታል በህክምና ሲከታታሉ ቆይተው በዛሬው እለት በ82 አመታቸው ማረፋቸው የኢትዮያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የህዝብ ግንኙነት ጠቅሷል፡፡


በቀድሞ ስማቸው ሊቀ ሥልጣናት አባ ሐረገ ወይን ገብረ ሥላሴ ተብለው የሚጠሩት ብፁዕ አቡነ ሰላማ በትግራይ ክልል በመቀሌ ከተማ ልዩ ቦታው በዓታ ለማርያም በተባለው ቦታ 1934 ዓ.ም መወለዳቸወን የህይወት ታሪካቸው ያስረዳል፡፡


ፊደልና ንባብና የቃል ትምሕርት በመማር ለግብረ ዲቁና የሚያበቃቸውን ትምሕርት ከየኔታ ክንፈ ገብርኤል በመማር ማዕረገ ዲቁናን ከብፁዕ አቡነ ማርቆስ ተቀብለዋል።


ብፁዕ አቡነ ሰላማ ፣ በትግራይ ፣ በጎንደር ፣ በጎጃም ከሚገኙ ሊቃውንት ዜማ ፣ ቅኔ የመፅሐፍት ትርጓሜ አጠናቀውናወንበር ዘርግተው ሲያስተምሩ ቆይተዋል፡፡


በመምህርነታቸው በተለይ በአርሲ ለ22 አመታት አስተምረው በርካታ ደቀ መዛሙርትን አፍርተዋል፡፡


ብፁዕ አቡነ ሰላማ በሊቀ ሥልጣናት ማዕረግ የቅድስት ሥላሴን ካቴድራል ፣ የሰዓሊተ ምህረትን የደብረ አሚን ተክለ ሃይማኖትንና ሌሎችንም አብያተ ክርስትያናት በአስተዳዳሪነት አገልግለዋል፡፡


ለጵጵስና ማዕረግ ከበቁም በኋላ የአክሱም ፅዮን የምስራቅ ሐረርጌ ሊቀ ጳጳስ ሆነው አገልግለዋል፡፡


እስከ እለተ እርፍታቸውም የታዕካ ነገስት በዓታ ለማርያምና የመንበረ መንግስት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ጠባቂ ሊቀ ጳጳስ ሆነው በማገልገል ላይ ነበሩ፡፡


ብፁዕ አቡነ ሰላም ቤተ ክርስቲያኗ አሉኝ ከምትላቸው ሊቃውንቶች አንዱ እንደነበሩ ተነግሯል።


Commentaires


bottom of page