top of page

መስከረም 14፣2017 - የጉራጌ ዞን በዘንድሮው የመስቀል በዓል ከ800,000 በላይ ጎብኚዎችን ለመቀበል ዝግጅቴን ጨርሻለሁ አለ

የመስቀል በዓል በሰፊው የሚከበርበት የጉራጌ ዞን በዘንድሮው በዓል ከ800,000 በላይ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር ጎብኚዎችን ለመቀበል ዝግጅቴን ጨርሻለሁ አለ፡፡


የ2017 እቅድ ከአምናው ጋር ሲነፃፅርም የ40 በመቶ ጭማሪ እንዳለው ተነግሯል፡፡


ይህንን የተናገረው የጉራጌ ዞን ባህል ቱሪዝም መምሪያ ነው፡፡


ዞኑ መስቀልን አስታኮ የሚያዘጋጀው ፌስቲቫል መኖሩም የተነገረ ሲሆን ለሰባተኛ ጊዜ ከመስከረም 11 ቀን ጀምሮ እንዳሰናዳ ተናግሯል፡፡


ከዓመት ዓመት በዞኑ ያለው የቱሪዝም ፍሰት እየተስተካከል እና እየጨመረ መምጣቱን ሰምተናል፡፡


በዘንድሮው የመስቀል በአል ከእደ ጥበብ ዘርፉ 1.5 ሚሊየን ብር ለመሰብሰብ የታቀደ መሆኑም የተነገረ ሲሆን በአጠቃላይ 100 ሚሊየን ብር ገደማ ለማግኘት እየተሰራን መሆኑን ሰምተናል፡፡


ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ይህንን ይጫኑ…


ፋሲካ ሙሉወርቅ

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page