የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በ2016 ዓ.ም ታጣቂዎች ከለላ ተደርጎላቸው በምክክሩ እንዲሳተፉ የማድረግ አቅሙ አለኝ ብሎ ነበር።
ተሳካለት ይሆን?
ታጣቂዎች እና በኮሚሽኑ ላይ የግልጽነት፣ ተዓማኒነት እና ገለልተኝነት ጣያቄ አለን በማለት ከምክክር ሂደቱ ራሳቸውን ያገለሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች በምክክር ሂደቱ እንዲሳተፉ ከቀይ መስቀል፣ ከአለም አቀፍ ተቋማት እና ኤምባሲዎች ጋር እየሰራ እንደሆነ በወቅቱ አስረድቷል፡፡
የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በተደጋጋሚ በግጭት ውስጥ ያሉ ሁሉም አካላት እና በምክክሩ እንዲሳተፉ ካልተደረገ የሚጠበቀው ውጤት ላይመጣ እንደሚችል በተደጋጋሚ እየተናገረ ነው።
በኮሚሽኑ ላይ የግልጽነት ታዓማኒነት እና ገለልተኝነት ጥያቄ አለን በማለት ከምክክር ሂደቱ እራሳቸውን ያገለሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ካልተሳተፉ ሀገሪቱ እየታመሰች ያለቸው በልሂቃን ስለሆነ ምክክሩ ውጤት ሊርቀው ይችላል ብሏል፡፡
የምክክር ኮሚሽን በበኩሉ እስካሁን ከምክክር ሂደቱ ራሳቸውን ያገለሉ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ሆኑ ታጣቂዎች እየተሳተፉ አይደለም ሲል ተናግሯል፡፡
ያሬድ እንዳሻው
Comments