ኢትዮጵያ የገንዘብ ሥርዓቷን በፍጥነትና በተለዋዋጭ ፖሊሲዎች እያሻሻለች መምጣቷን ተከትሎ ቢዝነስ ስራ ኢንቨስትመንት እና ሌላው የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ከነበረበት ጠባይ ውጪ እየተጓዘ ነው፡፡
ወትሮም ቢሆን ከውጭ ምንዛሪ ጋር በተገናኘ በይጨምራል ሀሳብና ያልተገመተ የንግድ ጠባይ የጥቁር ገበያው እየገነገነ መጥቶ ቆይቷል።
ይህን የተረዳው ብሔራዊ ባንክ የተለያዩ የገንዘብ ለውጥ ፖሊሲዎችንና የውጭ ምንዛሪ አስተዳደሮች ላይ ማሻሻያ አድርጓል።
ከዚህ መሀል ብሔራዊ ባንክ ነፃ የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች ያለማንም የባንክ ግንኙነት በተናጠል ፈቃድ እየሰጠ ነው።
በዚህ ረገድ የብሔራዊ ባንክን መስፈርት አማልቶ ኢትዮ ፎሬክስ የተባለ ድርጅት ነፃ የውጭ ምንዛሪ ቢሮ ለመክፈት ፈቃድ ማግኘቱን ለሸገር ራዲዮ ነግሯል።
የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ኤፍሬም ተስፋዬ በሁለት ቀን ውስጥ ወደ መደበኛ ስራ እንደሚገቡ አስረድተዋል።
ተህቦ ንጉሴ
Comments