መስከረም 12 2018 ከዛሬ ጀምሮ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ለጎብኚዎች ክፍት ይሆናል ተባለ፡፡
- sheger1021fm
- Sep 22
- 1 min read
የህዳሴ ግድብ ለመጎብኘት ምዝገባ ከዛሬ ጀምሮ ማድረግ ይቻላል ተብሏል፡፡።
ለጉብኝት ጉዞ የሚደረገው በኢትዮጵያ አየር መንገድ በኩል እንደሆነም ተነግሯል፡፡
ለጉብኝት መሄድ የሚቻለው ከ50 ሰው ጀምሮ እንደሆነም ሰምተናል፡፡

ጉዞ ማድረግ የሚቻለው ደርሶ መልስ እንደሆነም የቱሪዝም ሚኒስትሯ ሰላማዊት ካሳ ተናግረዋል ፡፡
በዚህም የታላቁ የህዳሴ ግድብ መጎብኘት የምትፈልጉ ከዛሬ ጀምሮ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ትኬት ቢሮዎች መመዝገብ ትችላላችሁ ተብሏል፡፡
ከግለሰቦች በተጨማሪም ተቋማት፣ የተለያዩ ጥናት አድራጊዎች፣ ተመራማሪዎች ጉብኝት ማድረግ እንደሚችሉ ሚኒስትሯ አስረድተዋል፡፡
አሁን ላይ የህዳሴ ግድቡን መጎብኘት የሚቻለው በኢትዮጵያ አየር መንገድ በኩል ብቻ እንደሆነም ተነግሯል፡፡
ለዚሁ ሲባልም በሳምንት ሁለት ቀን በረራ እንደሚኖር ሰምተናል፡፡
ማርታ በቀለ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s












Comments