top of page

መስከረም 12 2018 - በከምባታ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ (የማሳላ በዓል) እየተከበረ ነው፡፡

  • sheger1021fm
  • Sep 22, 2025
  • 1 min read

በከምባታ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ (የማሳላ በዓል) እየተከበረ ነው፡፡


የከምባታ ብሔር የዘመን መለወጫ የማሳላ እንግዶች ተገኝተው በዋናነት እየተከበረ ያለው  በከምባታ ዞን ዱራሜ ከተማ ነው፡፡

በዓሉ ትናንት የጀመረ ሲሆን በዛሬው እለትም  በከምባታ ሁለገብ ስቴዲየም በተለያዩ ዝግጅቶች ቀጥሏል።

በከምባታ ማህበረሰብ ዘንድ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው የማሳላ በዓል በናፍቆት የሚጠበቅና በከፍተኛ ዝግጅት  የሚከበር በዓል ነው ተብሏል፡፡


የብሔሩ ተወላጆች በማሳላ በዓል በግጭት ውስጥ ሆኖ አዲስ ዓመትን መቀላቀል የለባቸውም ተብሎ ስለሚታመን በሀገር ሽማግሌዎች የተጣሉትን የማስታረቅ ሥርዓትም ይከናወናል።


የመሳላ የበዓል አከባበር በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎችም  የሚቀጥሉ ይሆናል።


ማርታ በቀለ

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page