መስከረም 11፣2017 - ሰላም ሳይኖር ሀገራዊ ምክክር እንዴት ይሳካል?
- sheger1021fm
- Sep 21, 2024
- 1 min read
በኢትዮጵያ የሰላሙ ነገር መልክ ሊይዝ አልቻለም፡፡
ነፍጥ አንግበው ከመንግስት ጋር የሚዋጉ ታጣቂ ቡድኖች አሉ፡፡
በየአካባቢው ሰው የሚያግቱ፣ የሚዘርፉ፣ የሚገድሉ፣ ሰላም የሚያውኩ ግለሰቦች፣ ቡድኖች አሉ፡፡
በሌላ በኩል ሀገር የሚያግባቡ ጉዳዮች ላይ መክራ ብሔራዊ መግባባት በመፍጠር ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት ጉዞ ላይ ነች፡፡
የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በሀገሪቱ ያለው የሰላም እጦት የታሰበውን ሀገራዊ ምክክር ጠልፎ እንዳይጥለው ስጋት እንዳለው በተደጋጋሚ እየተናገረ ነው፡፡
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በበኩሉ የፀጥታ ችግሩ ተፅዕኖ እንዳለው አምናለሁ፣ መፍትሄ እንዲሰጥም መጠየቄን አላቋርጥኩም ብሏል፡፡
ያሬድ እንዳሻው
Comments