መስከረም 11፣2017 - ለማህበረሰብ በጎ ሰርተዋል፣ በቢዝነስ ስራ ፈጠራ በስፖርትና ኪነ ጥበብ የተሻለ ፈፅመዋል በሚል መስፈርት በየዓመቱ እጩዎችን የሚያስታውሰው የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ ከወዲሁ ስንዱ መሆኑ ተሰምቷል
- sheger1021fm
- Sep 21, 2024
- 1 min read
ለማህበረሰብ በጎ ሰርተዋል፣ በቢዝነስ ስራ ፈጠራ በስፖርትና ኪነ ጥበብ የተሻለ ፈፅመዋል በሚል መስፈርት በየዓመቱ እጩዎችን የሚያስታውሰው የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ ከወዲሁ ስንዱ መሆኑ ተሰምቷል፡፡
ማህበረሰብን አንፀዋል በሚል ሽልማቱን ለማበርከትም አምስት ሴት የሀገር ሰዎች ተለይተዋል ተብሏል፡፡
ይህንን ወሬ ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 የነገሩት የአፍሪካን ኢምፓክት አዋርድና የግራንድ አፍሪካ ራን ማኔጅመንት ዳይሬክተር ጋሻው አብዛ(ዶ/ር) ናቸው፡፡
በዚሁ የማስታወሻ ሽልማት ጋዜጠኛ መዓዛ ብሩ፣ ድምፃዊት አስቴር አወቀ፣ አትሌት ትዕግስት አሰፋ እና አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ እንዲሁም በቢዝነስ ዘርፉ እርብቃ ሀይሌ ተሸላሚ መሆናቸው አዘጋጆቹ ተናግረዋል፡፡
ይህ ዝግጅት በ2024 በአሜሪካ ሜሪላንድ ይካሄዳል፡፡
በእለቱ የዲሲ፣ ሜሪላንድና ቨርጂኒያ ባለስልጣን ሴናተሮች፣ ከንቲባና ሌሎችም ሀላፊዎች ይገኛሉ ተብሏል፡፡
እጩ ተሸላሚዎቹ በእለቱ በመገኘት ማስታወሻቸውንም እንደሚቀበሉ አዘጋጆቹ ነግረውናል፡፡
ተህቦ ንጉሴ
Comments