top of page

መስከረም 10፣2017 - የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና ከተማ የሆነችው ኦሞራቴ በቱርካና ሐይቅ የመዋጥ አደጋ ተጋርጦበታል ተባለ

  • sheger1021fm
  • Sep 20, 2024
  • 1 min read

ከ4 ዓመት በፊት(በ2012 ዓ.ም) ከ40 ኪሎ ሜትር በላይ ይርቃት የነበረው የቱርካና ሐይቅ በዙ ቀበሌዎችን እየዋጠ አሁን ከከተማዋ በ1.5 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ እንደሚገኝ ተነግሯል፡፡


የሐይቁ ውሃ አካባቢውን እየወጣ የተቃረባት የኦሞራቴ ከተማ በውሃው ለመዋጥ ተቃርባለች፡፡


የቱርካና እና የኦሞ ወንዝ እየሞሉ መጠናቸው እየጨመሩ የመጡበት ምክንያት ተለይቶ በጊዜ መፍትሄ ካልተሰጠው የኦሞራቴ ከተማ ህልውና አደጋ ላይ መሆኑን የዳሰነች ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ታደለ ሀብቴ አስረድተዋል፡፡


በዚህም የፌዴራል መንግስት 79,000 ሰዎች የተፈናቀሉበትን የኦሞ ወንዝ እና የቱርካና ሐይቅ መጥለቅለቅ ጉዳይ በየጊዜው ለምን የውሃ መጠናቸው እየጨመረ እንደመጣ በጥናት ለይቶ መፍትሄ እንዲሰጠው የዞኑ አስተዳዳሪ ጠይቀዋል፡፡


በ2017 በጀት ዓመት የቱርካና ሐይቅና የኦሞ ወንዝ ጉዳይ የፌዴራል መንግስትና የክልሉ መንግስት መፍትሄ ካልሰጡት የኦሞራቴ ከተማ ሙሉ በሙሉ በቀጣይ ክረምት በውሃ ልትሸፈን እንደምትችል አስተዳዳሪው አስረድተዋል፡፡


ያሬድ እንዳሻው

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page