top of page

መስከረም 10፣2017 - የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የተመሰረተበት ታሪካዊው ስፍራ እድሳት ተደርጎለት ለህዝብ ክፍት ሊሆን ነው

  • sheger1021fm
  • Sep 20, 2024
  • 1 min read

ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ከኬንያው ፕሬዝዳንት ጆሞ ኬንያታ፣ ከጋናው ፕሬዝዳንት ኩዋሜ ንኩሩማህ፣ ከግብጹ ፕሬዝዳንት ጋማል አብዱል ናስር፣ ከታንዛኒያው ፕሬዚዳንት ጁሊየስ ኔሬሬ፣ ከጊኒው ሴኮ ቱሬ እና ከሌሎችም መሪዎች ጋር በመሆን ነበር የቀድሞውን #የአፍሪካ_አንድነት_ድርጅት የአሁኑን የአፍሪካ ህብረት ግንቦት 20 ቀን 1955 ዓ.ም የመሰረቱት፡፡


የዛሬ 61 ዓመት የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን ለመመስረት እነዚህ የህብረቱ መስራቾች ፊርማቸውን ያኖሩት በአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን( #ECA ) ቅጥር ግቢ ውስጥ ያለውና ''African Hall'' በመባል በሚታወቀው ህንፃ መሰብሰቢያ አዳራሽ ነበር፡፡


ቦታው የህብረቱ መመስረቻ በመሆኑ ታሪካዊ ከመሆኑም ባሻገር ሌሎች ቅርሶችንም የያዘ ነው።


ቅርሶቹ በእርጅና ብዛት ከጥቅም ውጭ ከመሆናቸው በፊት እድሳት ያስፈልጋቸዋል ተብሎ በመታመኑ የቅርሱ ባለቤት የሆነው የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ላለፉት 2 ዓመታት እድሳት ሲደረግላቸው ቆይቷል፡፡


ኮሚሽኑ የህንፃውን ግንባታና በውስጡ የያዘውን #ታሪካዊ_ቅርሶች ለመገናኛ ብዙሃን አስጎብኝቷል።


የግንባታው የሲቪልና የአርኪቴክቸራል ስራዎች ተቆጣጣሪ የሆኑት አቶ ጌታቸው አርአያ ህንፃው ታሪካዊነቱ እንደተጠበቀ ተገንብቶ በመጠናቀቅ ላይ መሆኑን ነግረውናል።


የእድሳት ስራውን ለመከወን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት 57 ሚሊዮን ዶላር ተመድቦ ሲሰራ መቆየቱን የሚናገሩት አቶ ጌታቸው የፊታችን ጥቅምት ወር ሙሉ ለሙሉ ተጠናቅቆ ለህዝብ ክፍት እንደሚሆን ጠቁመዋል፡፡


ሙዚየሙ ለህዝብ ክፍት ሲሆን በውስጡ ምን ምን ያካትታል? የሚለውን ሃላፊው ሲያብራሩ ከህንፃው ቅርስነት ባለፈ የሜተር አርቲስት #አፍወርቅ_ተክሌ ስዕል ጨምሮ 7 የሚደርሱ የአፍሪካን መልኮች የሚገልፁ ስዕሎች ለእይታ ይቀርባሉ ብለዋል፡፡


የመልሶ ግንባታ የሥነ ስዕል እድሳት ስራዎቹ ከውጭ ሃገራት በመጡ ባለሙያዎች ተከውነዋል፣ የተቀሩት የሥዕል ስራዎች እድሳት ደግሞ በ #አለ_ፈለገ_ሰላም_የሥነ_ጥበብ_ተማሪዎች መከወኑን በአዲስ አበባ የሥነ ጥበብ ትምህርት ቤት የአለ ፈለገ ሰላም መምህር የሆኑት ሰዓሊ ሀይሉ በዛብህ ነግረውናል፡፡


ምንታምር ፀጋው

Comentários


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page