በዶሮ መኖ ላይ የቫት ክፍያ በመጨመሩ እና በሌሎችም ምክንያቶች በዘርፉ የተሰማሩ አምራቾች ኪሳራ እንደገጠማቸው እና ከገበያም እየወጡ መሆኑ ተነገረ።
በዶሮ መኖ ላይ ቫት መጨመሩ የመኖ እና የማምረቻ ዋጋ መጨመርም በገበያው ላይ የእንቁላል ዋጋም እንዲጨምር ምክንያት ሆኗል ተብሏል።
የኢትዮጵያ ዶሮ አርቢዎች እና አቀናባባሪዎች ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ ዝናው ፀሐይነህ ከዚህ ቀደም የእንቁላል እና የዶሮ ምርት በገበያ ላይ ከፍተኛ እንደነበር አንስተው አሁን ላይ ግን በተለይ የዶሮ መኖ ላይ ቫት እንዲኖር ከተወሰነ በኋላ አምራቾች ክፉኛ እንደተፈተኑ ነግረውናል።
የዶሮ መኖ ዋጋ የጨመረበት ምክንያትም ከውጪ የሚገቡ የመኖ የማቀነባበሪያ ግብአቶችን ለማስገባት የዶላር እጥረት ስላለ እንደሆነም ሰምተናል።
ከሀገር ቤት ከሚጠቀሙበት ግብዓት መካከል የሆነው የበቆሎ እጥረትም መኖሩን ሰምተናል።
በሌላ በኩል በተለያዩ አካባቢዎች ባለው የፀጥታ ችግር ምክንያትም የተመረቱ ምርቶችም ወደ ተለያዩ አካባቢዎች ለማዳረስ እንደተቸገሩም አቶ ዝናው ነግረውናል።
ፍቅሩ አምባቸው
Comments