top of page

ሐምሌ 9፣ 2016 - ኦፌኮ ‘’ሁሉን አቀፍ የጋራ መንግስት’’ ያለው ወይም ‘’የሽግግር መንግስት’’ እንዲመሰረት ፍላጎት እንዳለው መናገሩ ተሰምቷል

  • sheger1021fm
  • Jul 16, 2024
  • 1 min read

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ(ኦፌኮ) ሶስተኛው አጠቃላይ የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባን በማድረግ በተጓደሉ መሪዎች ምትክ የአመራር ሽግሽግ ማድረጉንና፤ በኦፌኮ አጠራር ‘’ሁሉን አቀፍ የጋራ መንግስት’’ ያለው ወይም ‘’የሽግግር መንግስት’’ እንዲመሰረት ፍላጎት እንዳለው መናገሩም ተሰምቷል፡፡


ፓርቲው በጠቅላላ ጉባኤው መንግስት በአስቸኳይ ከታጠቁ ሀይሎች ጋር የጀመረውን ጦርነት ትቶ ሰላም ለማውረድም ንግግር ማድረግ ይገባዋል ሲልም ጥሪ አቅርቧል፡፡


የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊው አቶ ሱልጣን ቃሲም ለሸገር እንደተናገሩት መንግስት በኦሮሚያና በአማራ ክልል ውስጥ ከፍተኛ ጦርነት እያካሄደ ይገኛል፡፡


ከጦርነት ወጥቶ የሰላም ንግግር ማድረግ እንዳለበትና አጠቃላይ ኦፌኮ አለ የሚለውን ችግሮች የህዝብ ግንኙነት ሀላፊው ተናግረዋል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ…



Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page