top of page

ሐምሌ 9፣ 2016 - ኢትዮጵያ ለማካሄድ ያሰበችው የሀገራዊ ምክክር ምን ያህሉ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በሂደቱ ተሳታፊ ሆነው ይሆን?

  • sheger1021fm
  • Jul 16, 2024
  • 1 min read


‘’በሀገራዊ ምክክር ሂደት ውስጥ ጉልህ ሚና ያላቸው ባለ ድርሻ አካላት ካልተሳተፉ የምክክር ሂደቱ እንደማይሳካ የሌሎች ሀገራት ተሞክሮ ያሳያል’’ ሲል የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተናግሯል፡፡


ኮሚሽኑ በምክክር ሂደት ውስጥ ያለፉ ሀገራት ውጤታማ እንዳይሆን ምክንያት ናቸው ያላቸውን ጉዳዮች ዘርዝሯል፡፡


ከእነዚህም ውስጥ በተለያዩ ቡድኖች መካከል እጅግ ሰፊ የሆነ የሃይል አለመመጣጠን ሲኖር እና የገነኑ ሀይሎች አቅማቸውን ተጠቅመው የሀገራዊ ምክክሩን የማስቀየር አዝማሚያ ሲያሳዩ ቀዳሚ ነዉ፡፡


በምክክር ሂደት ውስጥ ጉልህ ድርሻ ሊኖራቸው የሚችሉ ባለድርሻ አካላት በአግባቡ ተደራጅተው ሀሳባቸውን ማቅረብ ሳይችሉ ሲቀሩ እንዲሁም አንዳንድ ቡድኖች በሀገራዊ ምክክር ሂደት ውስጥ ለመሳተፍ ዝቅተኛን ፍላጎት አሊያም ሙሉ ለሙሉ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ከቀሩ የምክክር ሂደቱ ውጤት ላያመጣ እንደሚችል የሌሎች ሀገራት ተሞክሮ ያስረዳል ሲል ኮሚሽኑ ጠቁሟል፡፡


ኢትዮጵያስ ለማካሄድ ያሰበችው የአገራዊ ምክክር ምን ያህሉ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በሂደቱ ተሳታፊ ሆነው ይሆን?


ሸገር ኮሚሸነር ዮናስ አዳዬን ጠይቋል፡፡


ያሬድ እንዳሻው

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page