ጋዜጠኞችን ጨምሮ በሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ላይ፤ እንግልት እና ውክቢያ እንደሚፈጸም የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ተናግሯል፡፡
በሰብአዊ መብቶች ላይ የሚሰሩ የመብት ተሟጋቾች እንግልት እና ውክቢያ እንደሚፈጸምባቸው ኮሚሽኑ አረጋግጧል፡፡
በሀገሪቱ የሚንቀሳቀሱ 12 ሀገር በቀል የሰብአዊ መብቶች ድርጅቶች፤ ሰኔ 14 ቀን 2016 ዓ.ም ባወጡት የጋራ መግለጫ በመንግስት በኩል እየተፈጸሙ ያሉ ከልከላዎች፣ ጫናዎች እና ጥቃቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሱ ከመምጣት ይልቅ እየጨሩ መምጣታቸውን ተናግረው ነበር፡፡
እየተበራከቱ የመጡት ክልከላዎች እና ጥቃቶች ተስፋ ታይቶበት የነበረው የሲቪል ምህዳሩ ዳግም ወደ አስቸጋሪ ሁኔታ መመለሱን አመልካች ሆኖ እንዳገኙት በወቅቱ አስረድተዋል፡፡
ጥቃቱም በሰብአዊ መብቶች ድርጅቶች፣ በስራ ሃላፊዎች፣ በቦርዳ አመራሮች እና በሰራተኞች ላይ የሚፈጸም እንደሆነ የጋራ መግለጫቸው አስረድቷል፡፡
የዘፈቀደ እስራት፣ ማስፈራራት፣ ዛቻ፣ የድርጅቶቹን ቢሮ መስበር እና ንብረቶችን መውሰድ ደግሞ ከጥቃቶች ውስጥ ናቸው ብለዋል፡፡
በሀገሪቱ የሚንቀሳቀሱ መንግስታዊ ያልሆኑ የመብት ተሟጋች ተቋማት እየደረሰብን ነው ስላሉት በደል የጠየቅናቸው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ፤ መሰል ችግሮች መኖራቸውን አረጋግጠዋል፡፡
ምክትል ኮሚሸነሯ ጋዜጠኞችን ጨምሮ ሰብአዊ መብቶች ላይ የሚሰሩ ሰዎች ላይ እንግልት መኖሩን ተናግረዋል፡፡
‘’አናስገባም፣ መልስ አንሰጠም የሚሉ አመራሮች አሉ ይህ ምንም የማይካድ ነው፤ ግን የሰብአዊ መብቶችን ማስከበር እና ማስፋፋት ሂደት ነው’’ ብለዋል፡፡
ያሬድ እንዳሻው
Comentários