top of page

ሐምሌ 8፣ 2016 - ኢትዮጵያ ውስጥ የግብርና ኮሌጅ ከተከፈተ 70 ዓመት ያለፈው ቢሆንም ዛሬም እራሳችን መመገብ አልቻልንም

  • sheger1021fm
  • Jul 15, 2024
  • 1 min read

ኢትዮጵያ ውስጥ የግብርና ኮሌጅ ከተከፈተ 70 ዓመት ያለፈው ቢሆንም ዛሬም እራሳችን መመገብ አልቻልንም፡፡


በግርብርናው ዘርፍም በየዓመቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ከከፍተኛ ትምህርት የሚመረቁ ሲሆን ጥራቱ ላየው ግን ሁሌም ጥያቄ ይነሳል፡፡


በኮሎራዶ እስቴት ዩኒቨርስቲ መምህር የነበሩት ፕሬፌሰር አሰፋ ገብረ አምላክ ይህንን ሃሳብ ያጠናክራሉ፡፡


ኢትዮጵያ ውስጥ ባለፉት 30 ዓመታት 2 የነበሩት ዩኒቨርሲቲዎች አሁን ከ40 በላይ ከፍ ቢሉም የትምህርት ጥራት ግን አይታይም ይላሉ፡፡


‘’ወደ ዩኒቨርስቲ የገቡ ተማሪዎች የሚሰሩት ጥናትና ምርምር ማህበረሰቡን ያማከለ አይደለም’’ ያሉት ፕሮፌሰር አሰፋ ‘’መምህራኑም ቢሆን የሀገሪቱን ችግር የሚፈታ ምርምር እየሰሩ አይደለም’’ ሲሉ ይተቻሉ፡፡



Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page