በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሰረት፤ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ወቅት ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ ሰዎች ወደ ቀድሞ ቀያቸው እየተመለሱ ነው፡፡
ከራያ አካባቢ የተፈናቀሉ ሰዎች እየተመለሱ ያሉበት ሁኔታ ግን የትግራይ እና የአማራን ክልሎችን አላግባባ ብሏል፡፡
‘’በተፈናቃይ ስም ታጣቂዎች እየገቡ ነው’’ እያለ የአማራ ክልል ሲናገር የትግራይ ክልል በበኩሉ ‘’ታጥቀው እየገቡ ያሉት ከጦርነት በፊት የታጠቁ ናቸው ይህም ስምምነታችን ይፈቅዳል’’ ይላል፡፡
የራያ አላማጣዎቹ እንደሚሉት ከሆነ ተፈናቅለዋል የሚባሉ ሰዎች የስም ዝርዝር እንዳላቸው እና አሁን ይግቡ ከተባሉት ውስጥ ‘’ሀሰተኛ የሆነ የነዋሪነት መታወቂያ’’ የተዘጋጀላቸው እንዳሉም ተናግረዋል፡፡
የትግራይ ጊዜአዊ አስተዳደር በበኩሉ ''የ2012 እና 2013 ዓ.ም ታጥቀው የነበሩ፤ እና የተፈናቀሉ የታጠቁ ሚሊሻም ሆነ ፖሊስ ሲገቡ ምንም አይነት ተልእኮ እንደማይሰጣቸው የተናገረ ሲሆን ሌላ አካል ያስታጠቃቸው ካሉ ግን ትጥቃቸውን ፈትተው ይገባሉ'' ብሏል፡፡
‘’አሁን ተፈናቃዮቹ ይገባሉ ከተባለ ከዚህ ቀደም ደግሞ እየተዋጉ የገቡ የህወሃት ወታደሮች ይውጡልን’’ ሲሉ የራያ አላማጣ አስተዳዳሪ ጠይቀዋል፡፡
ማርታ በቀለ
Comentarios