top of page

ሐምሌ 8፣ 2016 - ''በኢትዮጵያ የንጹህ ውሃ ተጠቃሚ ሰዎች ብዛት 74.6 ሚሊዮን ድርሷል'' የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር

በኢትዮጵያ የንጹህ ውሃ ተጠቃሚ ሰዎች ብዛት 74.6 ሚሊዮን መድረሱን የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ተናገረ፡፡

ሚኒስቴር መ/ቤቱ ‘’ይህንን ከፍ ለማድረግ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን እየሰራሁ ነው’’ ብሏል፡፡


ይህ በቂ ስላልሆነ የውሃውንም ሆነ የኢነርጂውን እጥረት ለማስተካከል አቅጄ እየሰራሁ ነው ይላል፡፡


‘’ከዚህ ቀደም ያልተሰራበትና አሁን ያስጀመርኩት ክልሎች ሁሉንም ፕሮጀክቶች በራሳቸው እንዲያስፈጽሙ’’ እያደረገ መሆኑን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ተናግሯል፡፡


‘’ማህበረሰቡንም የስራው አንድ አካል በማድረግ ብዙ ሀብት የወጣበትን የመጠጥ ውሃ ግንባታ እንዳይባክንና በእኔነት ስሜት እንዲጠብቁት ማድረግ’’ ከተያዙ እቅዶች መካከል መሆናቸውን ሚኒስትሩ ዶ/ር ሀብታሙ ኢተፋ ተናግረዋል፡፡


በኢነርጂው ዘርፍም ቢሆን እስከአሁን 50 በመቶ የሚሆኑት ብቻ ተጠቃሚ የሆኑ ሲሆን የቀረውን የማህበረሰብ ክፍል ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል፡፡


በዚህ ስራ ከመንግስት በጀት በተጨማሪ የልማት አጋሮች ድጋፍ ቀላል እንዳልሆነ ሚኒስትሩ ተናግሮዋል፡፡



ማርታ በቀለ



Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page