top of page

ሐምሌ 8፣2015 - ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ የቢጂአይ ኢትዮጵያን ዋና መሥሪያ ቤት በጨረታ አሸንፎ እንደገዛው ተናገረ

ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ የቢጂአይ ኢትዮጵያን ዋና መሥሪያ ቤት በጨረታ አሸንፎ እንደገዛው ተናገረ፡፡


ድርጅቱ በአዲስ አበባ ሜክሲኮ የሚገኘውን የቢጂአይ ኢትዮጵያን ዋና መሥሪያ ቤት በጨረታ አሸንፎ አንደገዛው አና ለዚህም 1 ቢሊዮን ብር ቅድመ ክፍያ መፈጸሙን ጠቅሷል፡፡


ሙሉ ግዢው በስንት ብር እንደተፈጸመ የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር ፍሰሃ እሸቱ ከመግለጽ ተቆጥበዋል።


ቀሪ ክፍያዎች አንዳሉ ግን ሲናገሩ ሰምተናል፡፡


ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ከቢጂአይ ኢትዮጵያ በገዛው ቦታ ባለ 115 ወለል የከገበሬው ታወር እንዲሁም ለመኖሪያ፣ ለንግድ፣ ለመዝናኛ እንዲሁም፤ ለልዩ ልዩ አገልግሎቶች የሚውሉ 6 ሕንጻዎችን ለመገንባት ማሰቡን ተናግሯል፡፡


ፐርፐዝ ብላክ ልተገብረው ነው ብሎ ከተናገረው ለገበሬው ታወር ሼር ሆልደር ሞዴል ህንጻ ጋር በተያያዘ ብዙ ውዝግቦች ሲነሱ መቆየታቸው ይታወሳል።


ከዚህ አና ከቦታው ግዢ ጋር በተያያዘ የፌደራል ፖሊስ ምርመራ ማከናወኑን የተናገሩት ዶክተር ፍሰሃ በዚህም ምንም የህግ ጥሰት አለመፈጸሙ ተረጋግጠጧል ብለዋል፡፡



ንጋቱ ሙሉ



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

https://bit.ly/33KMCqz

Comments


bottom of page