የእርዳታ እህልን ጨምሮ ሊመዘበር የነበረ 2.8 ቢሊዮን ብርን ማዳን መቻሉን የስነምገባር እና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ተናገረ፡፡
ኮሚሽኑ ሊመዘበር የነበረ ከ2.8 ቢሊዮን ብር በላይ ገንዘብ፣ 8490 የአሜሪካን ዶላር እና ከ46.4 ሚሊዮን ካሬ ሜትር በላይ የገጠርና የከተነማ መሬት በተጠናቀቀዉ በበጀት ዓመት አድኛለዉ ሲል ለሸገር ነግሯል፡፡
በኮሚሽኑ የአስቸኳይ ሙስና መከላከል መሪ ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ገዛኸኝ ጋሻዉ፤ በተሰራ 1087 የአስቸኳይ መከላከል ስራ 2.8 ቢሊዮን ብር፣ 46.467 ሚሊዮን ካሬ ሜትር የመንግስትና የህዝብ ሀብት ከምዝበራ ድኗል ሲሉ ነግረውናል፡፡

የአስቸኳይ ሙስና መከላከል የተሰራባቸዉ ርዕሰ ጉዳይዎችም ግዢ ንብረት ማስውገድ የገጠር እና ከተማ መሬት እንዲሁም የእርዳታ እህል ነዉ ተብሏል፡፡
በምዝበራ ሂደትም ከበለሞያ እስከ የስራ ሃላፊዎች ድረስ ተሳትፈዋል ያሉት መሪ ስራ አስፈጻሚዉ ጉዳያቸዉ በህግ ተይዟል ብለዋል፡፡
ያሬድ እንዳሻው
Comentários