top of page

ሐምሌ 6፣2015 - የኢትዮጵያ ማዕድን በምቹ የግብይ ሥርዓት እንዲከናወን የሚያግዝ ዲጂታል መገበያያ ማዕከል ተከፈተ

የማዕድን ዲጂታል መገበያያ ማዕከልን ያስተዋወቀው በቀድሞ አጠራሩ “የኢትዮጵያ ማዕድን ነዳጅና ባዮፊውል ኮርፖሬሽን በአሁኑ መጠሪያው ደግሞ የኢትዮጵያ ማዕድን ኮርፖሬሽን ነው፡፡


ኮርፖሬሽን በማዕድን ዘርፍ ልማት ላለፉት 60 ዓመታት በውጭ ምንዛሪ ግኝት፣ በሰፊ ዕድል በፈጠራና በማህበረሰብ ልማት በርካታ ውጤቶችን ያስመዘገበ ተቋም መሆኑን የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ ራሄል ጌታቸው ተናግረዋል፡፡


የኢትዮጵያ ማዕድን ኮርፖሬሽን ከማዕድን ፍለጋና ልማት ሥራዎች በተጨማሪ የማዕድን ምርመራ ቁፋሮ (ድሪሊንግ)ና የማዕድን ላቦራቶሪ ፣ የማዕድን ጥናት አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል ተብሏል፡፡


ኮርፖሬሽናችን በትላንትናው ዕለት በዓይነቱ የመጀመሪያው የሆነውን የጌጣጌጥ ማዕድናት የኤሌክትሮኒክ ግብይት ሥርዓት ይፋ አድርጓል፡፡


ዲጂታል የግብይት ሥርዓት በመጠቀም ለጊዜው በጌጣጌጥ ማዕድናት ወደፊት ደግሞ ሌሎችንም ማዕድናት ለማስተዋወቅ ፣ ለመሸጥና ለመግዛት የሚያስችል መሆኑ ተነግሮለታል፡፡


ይህ አዲስ ዲጂታል የግብይት ሥርዓት ለማዕድን ላኪዎች የንግድ መዳረሻዎችን ለማስፋት የሚያግዝ እንዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃ የኢትዮጵያን ማዕድናት ለማስተዋወቅ ትልቅ ዕድል የሚፈጥር ነው ሲሉ የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ ተናግረዋል፡፡


ከዚህ በፊት በነበረው የጌጣጌጥ ማዕድናት የግብይት ሥርዓት ገዢና ሻጭን በተግቢው ደረጃ ለማገናኘት ከፍተኛ ችግር ያለበት፣ ግልጽኝነት የሌለውና ለኢ-መደበኛ የንግድ ሁኔታዎች የተጋለጠ መሆኑ ተነስቷል፡፡


የዲጂታል ማዕድን የግብይት ሥርዓቱ በዓለም ላይ የሚገኙ እንደ ኦፓል፣ ሩቢ፣ ኤመራልድ፣ ሳፋየር፣ እና ሌሎች በርካታ የጌጣጌጥ ማዕድን ዓይነቶችን ከሸማቾች ጋር እንዲያገናኝ ተደርጎ መሰራቱ ተጠቅሷል፡፡


በዚህም የእያንዳንዱን የጌጣጌጥ ማዕድን ባህሪያት፣ የጥራት ደረጃ ከየት አገርና ቦታ እንደተመረቱ መግለጫ አለው ተብሏል፡፡


የኢትዮጵያ ማዕድናት ዲጂታል የግብይት ሥርዓት በኢግል ላየን ቴክኖሎጂ ሲስተም ሶፍትዌሩ የተዘጋጀ ሲሆን ወጪው ደግሞ በዳሽን ባንክ እንደተሸፈነ ሰምተናል::ንጋቱ ሙሉየሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

https://bit.ly/33KMCqz

Comments


bottom of page