top of page

ሐምሌ 5፣ 2016 - የኢትዮጵያ አየር መንገድ የካርጎ ጭነት አውሮፕላን፣ የቱርክን የአየር ክልል እንዳይጠቀም ተከለከለ

  • sheger1021fm
  • Jul 12, 2024
  • 1 min read

ከሁለት ቀን በፊት መነሻውን ከቤልጂየም ሌጅ ከተማ አድርጎ ወደ አርመንያ ዋና ከተማ የረቫን ሲጓዝ የነበረው ቦይንግ 777 የካርጎ አውሮፕላን በቱርክ የአየር ክልል እንዳልፍ አየር ላይ መታገዱን ወርልድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡


ከቱርክ የመግቢያ ፈቃድ የተነፈገው የበረራ ቁጥር ET 3584 የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላኑ ወደ ቱርክ መዳረሻ በቡልጋርያ አየር ክልል ውስጥ ደጋግሞ ሲዘዋወር መታየቱን ዘገባው ጠቅሷል፡፡


በኋላም አውሮፕላኑ ወደ ቪየና ተመልሶ ካረፈ በኋላ የካርጎ ጭነቱ በሩሲያ በኩል ወደ አርመንያና ጆርጅያ መግባቱንም ተሰምቷል፡፡


የአሜሪካ የሲቪል አቪየሽን ኮሚቴ የኢትዮጵያ የካርጎ አውሮፕላን አስፈላጊ የይለፍ ፈቃድ እንደነበረው ጠቅሶ በመጨረሻው ሰዓት ቱርክ ክልከላ መጣሏን ለዜና ምንጩ ተናግሯል፡፡


ቱርክ እና አርመንያ በከረረ ቅራኔ ከገቡ በኋላ ቱርክ በአየር ክልሏ ወደ አርመንያ የሚያልፉ አይሮፕላኖችን ማገዷ ይታወሳል፡፡


ከዚህ ቀደምም የአሜሪካ አውሮፕላን በቱርክ በኩል ወደ አርመን እንዳያልፍ ታግዶ እንደነበር ዘገባው አስታውሷል፡፡


በጉዳዩ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ማብራሪያ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡


ትዕግስት ዘሪሁን

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page