top of page

ሐምሌ 5፣ 2016 - በኢትዮጵያ በተለያዩ ጉዳቶች የሚፈጠሩ አለመግባባቶች መፍትሄ እንዲያገኙ ወደ ፍርድ ቤቶች ማምራት የተለመደ ነው፡፡

ይህ ደግሞ ፍርድ ቤቶች ላይ ያለውን ጫና እያበረታው መሆኑን ይነገራል፡፡


በመሆኑም ወደ ፍርድ ቤቶች ከመሄድ አስቀድሞ አማራጭ የውዝግብ መፍቻ ዘዴዎችን መጠቀም አስፈላጊ ነው ተብሏል፡፡


‘’አማራጭ የውዝግብ መፍቻ ዘዴዎችን ህብረተሰብ ትስስርን ከመፍጠር አንፃር ያለውን ሚና’’ በሚል ሀሳብ ቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲ ባዘጋጀው የምርምር ፎረም ላይ ጥናታዊ ፅሁፍ ቀርቧል፡፡


አስቀድሞ አማራጭ የውዝግብ መፍቻ ዘዴዎችን እስካሁን ግን እየተሰራበት ያለው በንግዱ ማህበረሰብ ያሉትን አለመግባባቶች ለመፍታት ብቻ እንደሆነ በዝግጅቱ ጥናት ያቀረቡት ሚስጥረ መሃመድ ተናግረዋል፡፡


ይህ አካሄድ በሌሎች ዘርፎች ቢተገበር አሁን ካለንበት ችግር ልንወጣና ውጤታማ ልንሆን እንችላለንም ብለዋል፡፡


ፋሲካ ሙሉወርቅ



Comments


bottom of page