top of page

ሐምሌ 5፣ 2016 - በአዲስ አበባ በመንግስት የሚቀርበው ስኳር እየቀነሰ መጥቶ በወር ከ120,000 ኩንታል ወደ 39,000 ወርዷል ተባለ

ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች በመንግስት የሚቀርበው የስኳር መጠን እየቀነሰ መጥቶ በወር ከ120,000 ኩንታል ወደ 39,000 ኩንታል ወርዷል ተባለ፡፡


የከተማ አስተዳደሩ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ላሉ ነዋሪዎች ስኳርና ዘይትን ድጎማ በማድረግ በሸማች ህብረት ስራ ማህበራት በኩል እንደሚያቀርብ ይታወቃል፡፡


ይሁንና ይህ የሚቀርበው የድጎማ ምርት በተለይም የስኳር አቅርቦት መቀነሱን ሸገር ከአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ሰምቷል፡፡


ከዚህ ቀደም ከተማዋ 120,000 ኩንታል በየወሩ ይመደብላት የነበረ ቢሆንም፤ ከዚህ ዓመት አጋማሽ ጀምሮ የሚመደበው የስኳር መጠን እየቀነሰ መጥቶ አሁን በወር በአማካኝ 39,000 ኩንታል ወይም በዓመት ሲሰላ 468,000 ኩንታል ስኳር ለነዋሪው መቅረቡን ቢሮው ተናግሯል፡፡


ከዶላር ጋር በተገናኘ መንግስት እንደቀደመው ጊዜ በተመታጣኝ ዋጋ ስኳርን ከውጭ አምጥቶ ማከፋፈል እንዳልቻለ የሚያነሱት በቢሮው የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለ በዚህም ምክንያት በድጎማ የሚመጣው የስኳር ዋጋ በገበያው ላይ ካለው ጋር ተቀራራቢ ነው ብለዋል፡፡


በድጎማ የሚመጣው ስኳር በኪሎ 110 ብር ሲሸጥ በገበያ ላይ ደግሞ 120 ብር እየተሸጠ ነው፡፡


ስለዚህም ዋጋው በገበያው እንዲወሰን በማድረግ መንግስት በሂደት ከግብይቱ እንደሚወጣም አቶ ሰውነት ነግረውናል፡፡


ምንታምር ፀጋው



Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page