top of page

ሐምሌ 5፣ 2016 - ህንፃ ሲገነባ አካል ጉዳተኞችን ያማከለ እንዲሆን የሚያስገድድ ሆኖ የኢትዮጵያ የህንፃ አዋጅ መሻሻሉ ተሰማ

የትኛውም ህንፃ ሲገነባ አካል ጉዳተኞችን ያማከለ እንዲሆን የሚያስገድድ ሆኖ የኢትዮጵያ የህንፃ አዋጅ መሻሻሉ ተሰማ።


ተሻሽሎ የተሰናዳው የኢትዮጵያ የህንፃ አዋጅ አካል ጉዳተኞችን ሳያማክሉ ህንፃ የሚገነቡትን በህግ ለመቅጣት የሚያስችል መሆኑ ተነግሯል፡፡


አስገዳጅ መመሪያውን ተላልፈው በተገኙ አካላት እስከ ግንባታ ፈቃድ መነጠቅ የደረሰ እርምጃ ይጠብቃቸዋል ተብሏል።


የተሻሻለው ህግ ተግባራዊ ሲደረግ በተለይ አካል ጉዳተኞችን እየፈተነ ያለውን የህንፃ መወጣጫ ችግር እንደሚቀርፍ ታምኖበታል፡፡


እንደማንኛውም ማህበረሰብ የፈለጉትን አገልግሎት በቀላሉ ያለምንም ችግር እንዲያገኙ ሆነው ህንጻዎች እንዲገነቡ ህጉ ያስገድዳል።

በከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የመሰረተ ልማት ዘርፍ የሚኒስትር ዴኤታ ወንድሙ ሴታ አብዛኞቹ ህንፃዎች ሲገነቡ የሊፍት ወይንም የአሳንሰር ገጠማው ብዙ ጊዜ የሚካሄደው አካል ጉዳተኞችን ባላማከለ መልኩ በመሆኑ አካል ጉዳተኞች እንደማንኛውም የህብረተሰብ ክፍሎች የተለያዩ አገልግሎቶችን በቀላሉ እንዳያገኙ አድርጓቸዋል ብለዋል ።


አያይዘውም የዚህ የህግ ማቀፍ ማሻሻያ መዘጋጀትም ይህንን ችግር ለመቅረፍ እና አካል ጉዳተኞችን እኩል ተጠቃሚ ለማድረግም የታለመ ነው ሲሉ ተናግረዋል።


የህግ ማቀፉ በተለይ የአካል ጉዳተኞችን መብት ለማስጠበቅ ቢሆንም አሁን ላይ የሚስተዋሉ የአሳንሰር ገጠማ በጥራት ችግር እና በመሰል ምክንያትቶች በየህንፃዎች የሚከሰቱ ብልሽቶች በህብረተሰቡም የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ላይም መስተጓጎል የሚፈጥሩም አሉ የሚሉት ሚኒስትር ዴኤታው እነዚህን ችግሮች ጭምር ለመቆጣጠር ነው ህጉ መሻሻል ያስፈለገው ብለዋል።


በአዲስ ተሻሽሎ የተዘጋጀው የአሳንሰር(ሊፍት )ገጠማ ህግ በ 2017 ዓ.ም ፀድቆ ወደ ስራ እንደሚገባም ይጠበቃል።


ፍቅሩ አምባቸው

Comentarios


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page