top of page

ሐምሌ 5፣2015 - በግልገል በለስ አካባቢ ታጣቂዎች በፈጠሩት ጥቃት ንጹሃን ዜጎች እና የመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ ጉዳት መድረሱ ተነገረ

ከሰሞኑ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ግልገል በለስ አካባቢ ታጣቂዎች በፈጠሩት ጥቃት ንጹሃን ዜጎች እና የመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ ጉዳት መድረሱ ተነገረ፡፡


ጥቃቱ የደረሰው በአካባቢው ታጥቆ በሚንቀሳቀሰው የጉሙዝ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ በተባለ ታጣቂ ቡድን መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ተናግሯል፡፡


ኮሚሽነሩ ዶክተር ዳንኤል በቀለ አጠቃላይ የደረሰውን ጉዳት ለማጣራት ምርመራ እያደረግን ነው፤ ለጊዜው ግን ንጹሃን ዜጎች እና የመከላከያ ሰራዊት አባላት በታጣቂው መገደላቸውን አረጋግጠናል ብለዋል፡፡


አሁን በአካባቢው የመከላከያ ሰራዊት ተሰማርቶ መጠነኛ መረጋጋት ቢሰፍንም ውጥረቱ ግን እንደቀጠለ ነው ብለዋል ኮሚሽነሩ፡፡


በታጠቁ ቡድኖች መካከል በሚደርስ ጥቃት እና በመንግስት የፀጥታ ሀይል በሚወስደው የአፀፋ እርምጃ በመሃል ንጹሃን ዜጎች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት አሳሳቢ አድርጎታል ብለዋል፡፡


ዘላቂ መፍትሄም እንደሚያሻው አሳስበዋል፡፡



ትዕግስት ዘሪሁን



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

https://bit.ly/33KMCqz

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page