top of page

ሐምሌ 4 2017 - የአዲሱ የገቢ ግብር ረቂቅ አዋጅ ከተለያየ የገቢ ምንጭ የሚገኝ ገቢ አንድ ላይ ተጣምሮ ግብር እንዲከፈልበት ያደርጋል ተባለ

  • sheger1021fm
  • Jul 11
  • 1 min read

ይህም ማለት አንድ ሰው ተቀጣሪ ደመወዝተኛ ሆኖ በተጨማሪ የሚያከራየው ቤት ወይም ሌላ ንግድ ቢኖረው ሶስቱም ገቢው በአንድ ላይ ተሰልቶ ግብር ይከፈልበታል እንደማለት ነው፡፡


አሁን በስራ ላይ ባለው አዋጅ በተመሳሳይ ሰንጠረዥ ውስጥ ያሉ ብቻ በአንድ የሚጣመሩ ሲሆን በአዲሱ አዋጅ ግን ከሌላ ዘርፍም ቢሆን አንድ ግለሰብ ተጨማሪ ገቢ ካለው አንድ ላይ ተደምሮ ግብሩ ይሰላል ተብሏል።


ይህ ለውጥ ግለሰቦች በተበታተነ መንገድ ገቢያቸው ሲሰላ ተደጋጋሚ ከግብር ነፃ የሚሆን ተቀናሽን እያገኙ መንግስት ተገቢውን ገቢ እንዳያገኝ እያደረገ ስለሆነ ነው ተብሏል።


ከዚህ በተጨማሪም አንድ ሰው ከአንድ ምንጭ በሚያገኘው ገቢና ሌላ ሰው ከተለያየ የገቢ ምንጭ በሚያገኘው ተመሳሳይ ገቢ ላይ የሚከፈለው ግብር የተለያየ መሆኑ የፍታዊነት ጥያቄን የሚያስነሳ ስለሆነ እሱን ለማስተካከል ማሻሻያው አስፈልጓል ተብሏለ።


ይህ አሰራር ችግር ሊያስከትል ይችላል የሚል ጥያቄ ከህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ተነስቶበታል።


የገንዘብ ሚኒስቴር የስራ ሀላፊዎች ማሻሻያ የሚፈልጉ የገቢ ግብር አዋጁ ላይ ማሻሻያ መደረጉን አንስተው ይህኛው ክፍልም የግድ ማስተካከያ የሚፈልግ መሆኑን አብራርተዋል።

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..


ቴዎድሮስ ወርቁ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…



Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page