top of page

ሐምሌ 4፣ 2016 - የውጪ ጉዳይ ሚ/ር በቅርቡ ሹመት ለተሰጣቸው ቆንስላዎች፣ ዲፕሎማቶችና እጩ ምባሳደሮች ስልጠና መስጠት መጀመሩ ተናገረ

የኢትዮጵያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በተለያዩ አለማት ኢትዮጵያን ለሚወክሉ እና በቅርቡ ሹመት ለተሰጣቸው ቆንስላዎች፣ ዲፕሎማቶችና እጩ ምባሳደሮች ዛሬ በስካይ ላይት ሆቴል ስልጠና መስጠት መጀመሩ ተናገረ፡፡


የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ በቅርቡ ለተሾሙ የኢትዮጵያ ወኪሎች ስልጠና መጀመሩን ምክንያት በማድረግ ባደረጉት ንግግር በእውቀትና በጥበብ ያልተያዘ ዲፕሎማሲ የሀገርን ጥቅም ማስከበር ስለማይችል የሚሰጡ ስልጠናዎች አስፈላጊ ናቸው ብለዋል፡፡


ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሐምሌ 20 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ በሚዘልቀው የኢትዮጵያ ወኪሎች ስልጠና የተለያዩ የዲፕሎማሲ ክዕሎትን ያሳድጋል የተባሉ የስልጠና መርሃ ግብሮች መዘጋጀታቸውም አምባሳደር ታዬ ተናግረዋል፡፡


ከዚህ ቀደም ወደ ውጭ ሀገራት የሚደረገው የቆንፅላ፣ የዲፕሎማትና የአምባሳደርነት ሹመት ከውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ ሰራተኞች ውጪ ይደረግ የነበረ ሲሆን የዘንድሮ ሹመት በቀጥታ በውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት ውስጥ ለሚሰሩ ሰራተኞች የተሰጠ ሹመት በመሆኑ የተለየ ነው ሲሉም አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ ተናግረዋል፡፡

በቅርቡ ሹመት የተሰጣቸው የቆንፅላ ሀላፊዎች፣ ዲፕሎማቶችና እጩ አምባሳደሮች ብዛት 24 መሆኑ ታውቋል፡፡


የኔነህ ሲሳይ

Commentaires


bottom of page