የመንገድ መሰረተ ልማቶች ያልደረሰባቸውን እና ትርፍ አምራች አካባቢዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የመንገድ ስራ ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ፡፡
ፕሮጀክቱ በ5 ዓመት ውስጥ የሚጠናቀቅ ይሆናልም ተብሏል፡፡
ይህ የተባለው ዛሬ የከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር በሰጡት መግለጫቸው ነው፡፡
የገጠር መንገድ መሰረተ ልማት ስራ ለ12 ክልሎችና ለድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ጭምር ያካተተ መሆኑን ሰምተናል፡፡
ፕሮጀክቱን ለመከወን ወደ 300 ሚሊዮን ዶላር ከአለም ባንክ እርዳታ የተገኘ ሲሆን 107 ሚሊዮን ዶላር ደግሞ ከክልል መንግስታት በጀት የተውጣጣ ነው ተብሏል፡፡
በዚህም በድምሩ 407 ሚሊዮን ዶላር ለፕሮጀክቱ በጀት ተይዟል፡፡
ፕሮጀክቱ 126 ወረዳዎችን የሚያዳርስ ሲሆን 7554 ኪሎ ሜትር አዲስ መንገድ ግንባታ ፣ 10071 ኪሎ ሜትር የወረዳ መንገዶች ጥገና፣ 373 ተንጠልጣይ የእግረኛ መሻገሪያዎች እንዲሁም 715 የቆላማ አካባቢ መሸጋገሪያ ድልድዮች የሚገነቡ መሆኑን ሰምተናል፡፡
ፕሮግራሙ ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሏል፡፡
Comments