top of page

ሐምሌ 30 2017 - በተጠናቀቀው በጀት ዓመት አካባቢን በክለዋል በተባሉ 3,249 ተቋማት ላይ እርምጃ ተወስዶባቸዋል ተባለ

  • sheger1021fm
  • Aug 6
  • 1 min read

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት አካባቢን በክለዋል በተባሉ 3,249 ተቋማት ላይ እርምጃ ተወስዶባቸዋል ተባለ፡፡


ይህን ያለው የአዲስ አበባ ከተማ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ነው፡፡


ባለስልጣኑ በ2017 ዓ.ም አቅዶ የከወናቸውን ስራዎችን በተመለከተ ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥቷል፡፡


ባለስልጣኑ በመግለጫው ካነሳቸው ጉዳዮች መካከል የአካባቢ ብክለትን በተመለከተ አቅዶ የከወናቸው ስራዎች ይገኙበታል፡፡


በ2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማና አካባቢዋ ባሉ 14,872 አገልግሎት ሰጪና አምራች ተቋማት ላይ ክትትልና ቁጥጥር ማድረጉንም ባለስልጣኑ ተናግሯል፡፡

ree

በዚህም ክትትልና ቁጥጥር ካደረገባቸው ተቋማት ውስጥ 3,249 አገልግሎት ሰጪና አምራች ተቋማት አካባቢ ሲበክሉ ተገኝተዋል ብለዋል፡፡


ባለስልጣኑ በእነዚህ ተቋማት ላይ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያና የማሸግ እርምጃ እንደወሰደባቸውም ሰምተናል፡፡


እርምጃ ከተወሰደባቸው ውስጥ 3,066 ተቋማት ላይ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ ሲሰጣቸው 183 ተቋማት ደግሞ እንዲታሸጉ ተደርጓል ተብሏል፡፡


በባለስልጣኑ የማሸግ እርምጃ ከተወሰደባቸው ተቋማት መካከል 6 የፕላስቲክ ፋብሪካዎች፣ 23 የብሎኬት ፋብሪካ፣ 1 የሶፍት ፋብሪካ፣ 102 የምሽት ጭፈራ ቤቶች፣ 15 ጋራዥ ቤቶች፣ 1 ዘይት ፋብሪካ፣ 1 ማሽነሪና ብረታ ብረት አምራች ተቋም እንዲሁም 1 የቤትና የቢሮ እቃዎች ማምረቻ ድርጅት የማሸግ እርምጃ እንደተወሰደባቸው ሰምተናል፡፡


ባለስልጣኑ በእነዚህ እና በመሰል የደንብ ጥሰቶች 1.6 ሚሊየን ብር ከቅጣት መሰብሰቡንም ተናግሯል፡፡


ፍቅሩ አምባቸው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page