top of page

ሐምሌ 30፣2016 - የወለጋ ለ6 ዓመታት ከኤሌክትሪክ አገልግሎት ውጭ የነበሩ 143 ከተሞችና ቀበሌዎች አገልግሎት ማግኘት መጀመራቸው ተነገረ

  • sheger1021fm
  • Aug 6, 2024
  • 1 min read

በአራቱ የወለጋ ዞኖች ለ6 ዓመታት ከኤሌክትሪክ አገልግሎት ውጭ የነበሩ 143 ከተሞችና ቀበሌዎች አገልግሎት ማግኘት መጀመራቸው ተነገረ፡፡


በኦሮሚያ ክልል አራቱም የወለጋ ዞኖች 6 ዓመታት ከኤሌክትሪክ አገልግሎት ውጭ ሆነው የቆዩት በተከሰተው የፀጥታ ችግር ሳቢያ በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ላይ በደረሰ ውድመትና ጉዳት ነው ተብሏል፡፡


በተሰራው የመልሶ ጥገና ስራ ከኤሌክትሪክ አገልግሎት ውጭ የነበሩ 143 ከተሞችና ቀበሌዎች ዳግም ወደ አገልግሎቱ መመለሳቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተናግሯል፡፡

ዳግም አገልግሎት ያገኙት ቦታዎች፤ በምስራቅ ወለጋ ዞን 53 አካባቢዎች፣ በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን 36 ቀበሌዎች፣ በምዕራብ ወለጋ ዞን 35 አካባቢዎች እንዲሁም በቄለም ወለጋ ዞን 19 ቀበሌዎች በአጠቃለይ 143 የገጠር ቀበሌዎችና ከተሞች ናቸው ተብሏል፡፡


በአራቱም ዞኖች የተጎዱና የወደሙ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን መልሶ በመጠገን አገልግሎቱን ወደ ነበረበት ለመመለስ የሚደረገው ስራም እንደቀጠለም ተቋሙ ጠቅሷል፡፡


ማንያዘዋል ጌታሁን

Comentários


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page