የነሀሴ ወር 2016 ዓም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ሃምሌ ወር በነበረበት ይቀጥላል ተብሏል፡፡
የነሀሴ ወር 2016 ዓ.ም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ምንም የዋጋ ጭማሪ ሳይደረግበት ሃምሌ ወር በነበረበት የመሽጫ ዋጋ እንዲቀጥል መወሰኑ ተነግሯል፡፡
የነዳጅ ማደያዎች ካልተገባ የምርት ማከማቸት እና የዋጋ ጭማሪ ሳያደርጉ ተግባራዊ እንዲያደርጉ መታዘዛቸውን የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል፡፡
በነዳጅ ስርጭትና ሽያጭ ዙሪያ ጥብቅ ቁጥጥር እና ክትትል እንዲያደርግ ተመከሮ ስራዎች መጀመራቸውንም ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል፡፡
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz
Comments