top of page

ሐምሌ 3፣ 2016 - የግብርናውን ዘርፍ ወደ ዘመናዊ የአመራረት ዘዴ ለማምጣት እና ዘርፉ ያሉበትን ችግሮች ይፈታል የተባለለት ማህበር ተቋቋመ ተባለ

በኢትዮጵያ የግብርናውን ዘርፍ ወደ ዘመናዊ የአመራረት ዘዴ ለማምጣት እና ዘርፉ ያሉበትን ችግሮች ይፈታል የተባለለት ማህበር ተቋቋመ ተባለ፡፡


ማህበሩ በግብርናው ዘርፍ የተሰማሩ የግል አልሚዎች በአንድ የሚያገናኝ፣ ያሉባቸውን ችግሮች ሊፈታ የሚችል እና ምርታማነታቸውን እንዲጨምሩ የሚያደርጋቸው ይሆናል ተብሎለታል፡፡


የኢትዮጵያ ሰብል አምራቾች እና ላኪዎች ባለብዙ ዘርፍ ማህበር በሚል ከስምንት ወራት በፊት ተቋቁሞ የግል አልሚዎቹ ያሉባቸውን ችግሮች አቤት ማለት ጀምረዋል ተብሏል፡፡


የማህበሩ አባላት የሆኑት 5800 ባለሃብቶች፤ ከ2.2 ሚሊየን ሄክታር በላይ መሬት የያዙ መሆናቸውን የተናገሩት የማህበሩ ፕሬዘደንት አቶ መልካሙ አብርሃም ከያዙት መሬትም እያለሙ ያለው 41 ከመቶ ነው ብለዋል፡፡


ይህ ደግሞ በዘርፉ እየተከወነ ያለው አሰራር መቀየር እንዳለበት ያሳያል ያሉ ሲሆን ለዚህ እና ለሌሎች ችግሮቻችን መፍትሄ እንድናመጣ ማህበሩ ያግዘናል ይላሉ፡፡


ከዚህ ቀደም እንዲህ ዓይነት ማህበር አለመቋቋሙ ባለሃብቱንም ሆነ ዘርፉን ምን ያህል ጎዳው?


የማህበሩ መቋቋሙስ ምን መልካም ነገር ይዞልን ይመጣል?

ፋሲካ ሙሉወርቅ

Comentários


bottom of page