የሸጎሌ የቁም እንስሳት ገበያ ከቦታው አንዲነሳ በፍርድ ቤት የመጨረሻ ውሳኔ ተሰጠ፡፡
በመኖሪያ መንደር አካባቢ የተገነባውና በሚፈጥረው የአካባቢ ብክለት ነዋሪዎች ሲያማርሩበት የቆየው የገበያ ማዕከሉ ከዚህ ቀደምም ከቦታው እንዲነሳ በተከማዋ #ፍርድ_ቤት ጉለሌ ምድብ ችሎት ተወስኖበት ነበር፡፡፡
ተከሳሾች የጉለሌ ክፍለ ከተማ ንግድ ፅ/ቤት እና የኢትዮጵያ የቁም እንስሳት ነጋዴዎች ማህበር ይግባኝ ብለው ሲከራከሩ ቆይተዋል፡፡
የአካባቢውን ህዝብ ወክሎ ቁም ለአካባቢ የተሰኘው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅትም ለአምስት ዓመት በፍርድ ቤት ሞግቶ የመጨረሻ ውሳኔ ከትናንት በስትያ ተሰጥቷል፡፡
ገበያው #የአካባቢ_ብክለት ስለመፍጠር አለመፍጠሩ በገለልተኝነት ማስረጃ እንዲያቀርብ የተጠየቀው የፌዴራሉ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ብክለት ስለመኖሩ በማረጋገጡ ፍርድ ቤቱ ገበያው ከቦታው እንዲነሳ የመጨረሻ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡
ትዕግስት ዘሪሁን
Comments