top of page

ሐምሌ 29፣2016 - የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና ኢትዮጵያ በአፍሪካ ውስጥ ያለው ሰፊ የገበያ እድል እንድትጠቀም ያደርጋታል ተብሏል



ኢትዮጵያ ቡናን ወደ ውጪ በመላክ በዚህ ዓመት 1.43 ቢልዮን ዶላር ገቢ አግኝታለች፡፡


ይህ ገቢ የተገኘው የተላከው አብዛኛው ምርት በጥሬው ከአፍሪካ ውጪ ላሉ ሀገራት በመላክ ነው ተብሏል፡፡


ይህም የሆነው ደግሞ አሁን ያሉት #ቡና_ገዢዎች የኢትዮጵያን ቡና በጥሬው ብቻ መግዛት ስለሚፈልጉ መሆኑን ሰምተናል፡፡


ሰሞኑን የአፍሪካ ህብረት ቡናን የህብረቱ አንዱ ስትራቴጂክ እቅድ አድርጎታል ከተባለ ወዲህ ግን የቡና ገበያ ተስፋዎች እየታዩበት መሆኑን እየተነገረ ነው፡፡


#የኢትዮጵያ_ቡና_እና_ሻይ_ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ እንዳሉት አፍሪካ ወደ ውጪ የምትልከው የቡና ምርት 12 በመቶ እራሷ የምትጠቀመው የቡና መጠን ደግሞ 13 ከመቶ ነው ይህም ማለት የምትልከውና የምትጠቀመው የቡና ምርት መጠን የተመጣጠነ አይደለም፡፡


ይህንን ክፍተት ለመሙላት ከአፍሪካ ተልኮ በሌሎች ሀገራት እሴት የተጨመረበትን ቡና በውድ ዋጋ ወደ ራሷ መልሳ ታስገባለች ተብሏል፡፡


ኢትዮጵያ ከዚህ በፊት ቡናን ወደ አፍሪካ ሀገራት አትልክም ነበር ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ አሁን ይፋ የተደረገው ቡናን የአህጉሪቱ የ2063 ስትራቴጂክ እቅድ ለኢትዮጵያ ትልቅ እድል ይዞ መጥቷል ብለዋል፡፡


#የአውሮፓ_ህብረት በቅርቡ በቡና ላይ ያወጣው ህግ አፍሪካ እንደ አህጉር በአንድነት ለማሰማት ህብረቱ አልነበራትም ያሉት ዶክተር አዱኛ ከዚህ በኋላ ህብረቱ ችግሮችን በጋራ የሀገራቱን ሀሳብ ይዞ ይሟገታል የሚል ተስፋ አላቸው፡፡


የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና መኖሩ እና በአህጉሪቱ ካሉ ሀገራት 25 ሀገራት ብቻ ቡና አብቃይ መሆናቸው ኢትዮጵያ በአፍሪካ ውስጥ ያለው ሰፊ የገበያ እድል እንድትጠቀም ያደርጋታል ተብሏል፡፡


በተለይም እሴት የተጨመረበት ቡናን ለመላክና የራሷ #ብራንድ በመፍጠር የተሻለ ገቢ እንድታገኝ ይረዳታል ሲሉ የቡና እና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ነግረውናል፡፡


ኢትዮጵያ ይህንን እድል ለመጠቀም ዝግጁ ነች የተባለ ሲሆን ከምዕራባውያን የሚመጣውን ጫና ለመቋቋም እና የተሻለ የውጪ ምንዛሪ ለማግኘት እድሉን እንደምትጠቀምበት የዋና ዳይሬክተሩ ተስፋ ነው፡፡


በረከት አካሉ

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page