ቁጥራቸው የበዛ ባይሆንም የሀገር ውስጥ እና የውጪ ባለሀብቶች መሬት በመውሰድ በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የኢንቨስትመንት ስራ እየሰሩ መሆኑን ሰምተናል፡፡
ሀገሪቱ ወስጥ ባለው የፀጥታ ሁኔታ ጦርነትና ሌሎች የመሰረተ ልማት አቅርቦት ችግር ምክንያት ባለሀብቱ የጀመረው ስራ ለማቆም እንደሚገደዱ መረጃዎች ሲወጡ ይስተዋላል፡፡
ላለፉት 5 ዓመታት በአማራ ክልል በአበባ እርሻ ስራ ላይ ተሰማርቶ የነበረው ‘’አቢሲንያ ሆልቲ’’ በክልሉ በነበረው የፀጥታ ችግር ምክንያት ስራው ለማቆም ከተገደዱ ድርጅቶች አንዱ ነው፡፡
የድርጅቱ ተወካይ አበባየሁ ገብረስላሴ እንዳሉት፤ የመንገድ መዘጋት የመሰረተ ልማት እጦት እና ግጭት በክልሉ የነበራቸው የአበባ ስራ ለማቆም ተገደናል ብለዋል፡፡
አቢሲኒያ ሆልቲ በአማራ ክልል ያለው የአበባ እርሻ አሁን ላይ ወደ ምርት ገብቶ የመጀመሪያው ዙር የአበባ ምርት ለገበያ አቅርቦ የውጪ ምንዛሪ ማምጣት ጀምሮ ነበር ያሉት ወይዘሮ አበባየሁ ይህ ግን ባለፉት ወራቶች ተቋርጧል ይላሉ፡፡
ታዲያ ይህ ችግር ለማስተካከል ቅድሚያ መደረግ ያለበት መንግስት የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት መሟላት እና የፀጥታው ሁኔታ ማስተካከል አለበት ይህ ከሆነ ባለሀብቱ ስራውን በሚገባ በመስራት ለሀገር የውጪ ምንዛሪ ማስገኘት ይችላል ሲሉ ያሳስባሉ፡፡
ኢትዮጵያ በዚህ ዓመት የአበባ ምርት ወደውጪ በመላክ 566 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ያገኘች ሲሆን 63 ባለሀብቶች በዚህ ዘርፍ መሰማራታቸው መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
በረከት አካሉ
Comments