በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ያሉ ምሁራን ስራዎቻችንን ይነጥቀናል በማለት የዲጂታል ቴክኖሎጅውን ለመጠቀም እንደሚያመነቱ ጥናት አሳይቷል፡፡
ከፍተኛ የትምህርት ተቋማቱ አሁን እየተጠቀሙት ያለው አሰራር ከዚህ ቀደም ወረቀት ነክ የሆኑ አሰራሮችን ወደ ዲጂታል ከመቀየር በዘለለ ዲጂታል ቴክኖሎጅውን በመጠቀም የእለት ተእለት ስራዎቻቸውን መከወኑ ላይ አልበረቱም ተብሏል፡፡
ዲጂታል ቴክኖሎጅውን በመጠቀም ስራዎችን መከወን ላይ መንገድ ቢጀምሩም ግን አለመበርታቸው የተነገረ ሲሆን ለዚህ ደግሞ ሀገራዊም ተቋማዊም ችግሮች ጭምር አሉበት ተብሏል፡፡
ተማሪዎችን ዩኒቨርሲቲ ሳሉ ዲጂታል ቴክኖሎጅው ላይ ብቁ ማድረግ ካቻልን ወደ ገበያው ሲቀላቀሉ በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እና የፈጠራ ሰዎች መሆን ይቸግራቸዋል የሚሉት ጥናት አቅራቢው ይህ እንዳይሆን ደግሞ ቀድሞዉኑ በርትተን መስራት ይኖርብና ብለዋል፡፡
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በበኩሉ የዲጂታል ትምህርት እድገትን የተሻለ ለማድረግ አስተማሪዎቼን እያሰለጠንኩ ነው ብሏል፡፡
ፋሲካ ሙሉወርቅ
ความคิดเห็น