ኢትዮጵያ ከግማሽ በላይ የሚሆነው ህዝቧ በከፋ ድህነት ውስጥ እንደሚኖር ይነገራል፡፡
ለዚህም የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ሁኔታ ለድህነቱ መለኪያ ተደርገው የተቀመጡ በቂ የዕለት ገቢ አለመኖር፣ በቂ ምግብ ማግኘት አለመቻል፣ የንጹህ መጠጥ ውሃ አለመዳረስ፣ ህክምናና ትምህርት አለማግኘት ይጠቀሳሉ፡፡
የሀገሪቱን ዜጎች #ከድህነት ለመታደግ በተለያዩ ጊዜያት የፖሊሲ ለውጦች እና በድህነት ቅነሳ ላይ ያተኮሩ ስራዎች በመንግስት ይከናወናሉ፤ ነገር ግን አሁንም ቢሆን ይህ ዜጎችን ከድህነት አላስወጣም፡፡
በተጨባጭ በችግሩ ላይ የሚከወኑ ስራዎች #ለምን ለውጥ አላመጡም? ወይም ሲዘልቁ አይታዩም ስንል በኢትዮጵያ በድህነት ቅነሳ ላይ የሚሰራ አንድ ተቋም ጠይቀናል፡፡
ከድህነት መንስኤዎች አንዱ የሆነው በቂ ምግብ አለማግኘት ወይም የተመጣጠነ የአመጋገብ ሥርዓት አለመኖር በመለየት በጉዳዩ ላይ የተከወኑ በርካታ ፕሮጀክቶች ውጤት አልባ እንዲሆኑ ያደረጋቸው ምክንያት መለየት ላይ ጥናት መከወኑን የሚናገሩት በኢትዮጵያ በድህነት ቅነሳ እና ሌሎች የበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ የሚሰራው ‘’ኦፒየም ኢትዮጵያ’’ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሚካኤል አድነው ናቸው፡፡
በኢትዮጵያ ሊጠናቀቅ ጥቂት ጊዜያት በቀሩት 2016 ዓ.ም በድህነት ላይ የተከወነ ጥናት 61 በመቶ ያህል ኢትዮጵያውያን በከፋ ድህነት ውስጥ እንደሚኖሩ አሳይቷል፡፡
በጥናቱ 37 በመቶ ዜጎች በየዕለቱ #የጥሬ_ገንዘብ እጥረት እንደሚገጥማቸው፣ 26 በመቶ ያህሉ ደግሞ በቂ ንጹህ የመጠጥ ውሃና የህክምና አገልግሎት እንደማያገኙ ተጠቅሷል፡፡
ምህረት ስዩም
Comments