ሐምሌ 29፣2016 - በኢትዮጵያ የቀጠለው ግጭት የአካል ጉዳተኞችን በህይወት የመኖር መብት ጥያቄ ውስጥ እንዲገባ አድርጓል ተብሏል
- sheger1021fm
- Aug 5, 2024
- 1 min read
በኢትዮጵያ የቀጠለው ግጭት የአካል ጉዳተኞችን በህይወት የመኖር መብት ጥያቄ ውስጥ እንዲገባ አድርጓል ሲል የኢትዮጵያ የአካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን ተናገረ፡፡
በሀገሪቱ በተደጋጋሚ የተከሰቱ እና አሁንም የቀጠሉ ግጭቶች #አካል_ጉዳተኞችን ቀዳሚ ተጎጂ አድርጓቸዋል ሲል ፌዴሬሽኑ ተናግሯል፡፡
ጦርነት ግጭት እና አለመረጋጋት ሮጦ ማምለጥ የማይችለውን አካል ጉዳተኛ ለሞትና ለከፋ ጉዳት እየዳረገው መሆኑን የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አባይነህ ጉጆ ነግረውናል፡፡
#በህውሃት እና በፌደራል መንግስት መካከል በተደረገው ጦርነት በትግራይ ክልል የሚገኙ የአካል ጉዳተኛ ማህበራት የስራ ኃላፊዎች ሳይቀሩ መገደላቸውን ፕሬዝዳንቱ ነግረውናል፡፡
የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አባይነህ ጉጆ “ጦርነቱ ለቡዙ አካል ጉዳተኞች ፋብሪካ ሆኖ አልፏል” ብለዋል፡፡
“አሁንም ግጭት በጣም ትልቅ እንቅፋት ሆብናል ያሉት አቶ አባይነህ በሕይወት የመኖር መብታችን ጥያቄ ውስጥ ገብቷል” ሲሉ አስረድታዋል፡፡
“በራስህ አገር በተወለድክበት አገር ፈጣሪ የሰጠህ አገር ላይ እየኖርክ በሰላም እጦት ምክንያት የመኖርህ ጉዳይ ጥያቄ ውስጥ ከገባ ከዚህ በላይ ስጋት ያለም” ሲሉ ነግረውናል፡፡
#የኢትዮጵያ_ሰብዓዊ_መብቶች_ኮሚሽን በተደጋጋሚ ባወጣቸው ሪፖርቶች አካል ጉዳተኞች በግጭቶች ምክንያት ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰባቸው እንዳለ አስረድቷል፡፡
የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን በህይወት የመኖር መብታቸው ጥያቄ ውስጥ የገባውን አካል ጉዳተኞችን ችግር የተጀመረው ሃገራዊ የምክክር ሂደት ሀቀኛ ከሆነ መፍትሄ ያገኛል ብዬ እጠብቃለሁ ብለዋል፡፡
ያሬድ እንዳሻው
Comments