በኒጀር መንግስታቸው በወታደሮች የተገለበጠባቸው ፕሬዘዳንት ሞሐመድ ባዙም ወደ ሀላፊነታቸው ለመመለስ አሜሪካንን እርጂኝ ማለታቸው ተሰማ፡፡
በኒጀር የፕሬዘዳንት ሞሐመድ ባዙም መንግስት በወታደሮች ከተገለበጠ ከሳምንት በላይ ሆኖታል፡፡
ፕሬዘዳንቱ ወደ ሀላፊነቴ እንድመለስ እርዱኝ ያሉት በጦር አለቆቹ እገታ ውስጥ ባሉበት ሁኔታ በፃፉት ዘለግ ያለ መግለጫ ነው ተብሏል፡፡
ባዙም ግልበጣው ካልተቀለበሰ ለኒጀር ብቻ ሳይሆን ለመላ ቀጠናውም እጅግ አደገኛ ነው ማለታቸው ተጠቅሷል፡፡
በሌላ መረጃ የኒጀር ወታደራዊ የመንግስት ገልባጮች አገሪቱ ከፈረንሳይ ጋር የነበራትን የወታደራዊ ትብብር ስምምነት ከእንግዲህ አያሻንም ብለው አሽቀንጥረው መጣላቸው ተሰምቷል፡፡
ከዚህ ቀደም የማሊ እና የቡርኪናፋሶ መንግስታትም ተመሳሳይ እርምጃ እንደወሰዱ ዘገባው አስታውሷል፡፡

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz
Website: https://www.shegerfm.com/
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments