በአዲስ አበባ ከተማ ካሉ የግል ትምህርት ቤቶች፤ ከ80 በላይ የሚሆኑት በ2017 የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን ተቀብለው ማስተማር እንደማይችሉ መነገሩ ይታወሳል።
በመጭው ዓመት የማስተማር ስራውን እንዳይሰሩ #በታገዱ ትምህርት ቤቶችም 29,000 ተማሪዎች ሲማሩ እንደቆዩም ሰምተናል።
ይህን ተከትሎ በ2017 የትምርት ዘመን ተማሪዎችን የሚቀበሉ ትምህርት ቤቶች ላይ መጣበብ አይፈጠርም ወይ?
#በአንዳንድ ክፍለ ከተሞችም ይሄው ችግር እያጋጠማቸው እንደሆነ ሀላፊዎች ሲናገሩ ሰምተናል፡፡
የተማሪ ቁጥር መጨመርን ተከትሎም በአንዳንድ ትምህርት ቤቶች ላይ #የፈረቃ_ትምህርት ለመጀመር እንደሚገደዱ ተናግረዋል፡፡
ሸገር ኤፍኤም ራዲዮም፤ ይህንን እና ሌሎች ጥያቄዎችን በመያዝ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮን ጠይቋል፡፡
ፋሲካ ሙሉወርቅ
コメント