top of page

ሐምሌ 26፣2016 - ያመለጡ እስረኞችን ዳግም ለመመለስ እንቅስቃሴ እያደረኩ ነው ሲል የፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ተናገረ

ግጭት በተከሰቱባቸው አካባቢዎች ከማረሚያ ቤት ያመለጡ እስረኞችን ዳግም ለመመለስ እንቅስቃሴ እያደረኩ ነው ሲል የፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ተናገረ፡፡


በኢትዮጵያ በተከሰቱ ግጭቶች ምክንያት ሙሉ በሙሉ የወደሙ እና ጉዳት የደረሰባቸው ማረሚያ ቤቶች ጥቂት አይደሉም፡፡


በዚህም ከነብስ ግድያ እስከ ቀላል ወንጀል ፈፀመው በተለያዩ ማረሚያ ቤቶች የነበሩ ፍርደኞች፤ አጋጣሚዎቹን ተጠቅመው ማምለጣቸውን እየተነገረ ቆይቷል፡፡


ለአብነትም በአማራ ክልል ብቻ በተከሰተው ግጭት ምክንያት፤ 7,000 ታራሚዎች(እስረኞች) ከማረሚያ ቤቶች መበተናቸውን ክልሉ ሰሞኑን ባደረገው ዓመታዊ ጉባኤው ላይ ተናግሯል፡፡


በተለይ ግጭት በተደጋገመባቸው አማራ እና ትግራይ ክልሎች ከማረሚያ ቤቶች ያመለጡ ሰዎች፤ በየቦታው ዝርፍያን ጨምሮ በርካታ ወንጀሎችን እየፈፀሙ እንደሆነ የተለያዩ አካላት ሲናሩ ይሰማል፡፡

ሸገር በየቦታው ተበትነዋል ስለተባሉት እስረኞች ጉዳይ፤ የፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽንን ጠይቋል፡፡


የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ጄኔራል የኑስ ሙሉ፤ ‘’አንጻራዊ ሰላም ባለባቸው አካባቢዎች ያመለጡ እስረኞችን ዳግም ወደ ማረሚያ ቤቶች ለመመለስ ከአካባቢው የጸጥታ አካላት እና ከክልሎች ጋር እየተነጋገርን ነው’’ ብለውናል፡፡


‘’በማረሚያ ቤቶቹ የደረሰው ውድመት ከፍተኛ ነው ያሉት ኮሚሽነሩ፤ የተበተኑት እስረኞች መመለሱ በአንዴ ሳይሆን ቀስ በቀስ የሚሰራ’’ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡


‘’የወደሙት ማረሚያ ቤቶችን ለማቋቋም ለክልሎቹ በቁሳቁስም ሆነ በሌላውም ድጋፍ እናደርግላቸዋልን’’ ብለውናል፡፡

የውድመቱ መጠን ምን ያህል ነው ያልናቸው ሀላፊው፤ ‘’እስካሁን ቦታዎቹ ድረስ ሄድን ስላላየን ይህን ያህል ነው ብለን መናገር አንችልም’’ የሚል ምላሽ ሰጥተውናል፡፡


ያመለጡ ታራሚዎችን ለመመለስ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው ይባል እንጂ፤ በተለይ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች ለእስረኞች መበተን ዋነኛ ምክንያት የሆኑት ግጭቶች አሁንም እንደቀጡ መሆናቸው ይታወቃል፡፡


ማንያዘዋል ጌታሁን

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page