‘’ቢ ጂ አይ ኢትዮጵያ’’ ከመደበኛ የማምረት ስራው ጎን ለጎን የተለያዩ የማህበራዊ ሃላፊነት ስራዎችን እየከወነ እንደሚገኝ ተናገረ።
ኩባንያው ፋብሪካዎቼ በሚገኙባቸው አካባቢዎች ያሉ ነዋሪዎች የጤና እና የትምህርት አገልግሎት እንዲያገኙ የራሴን አስተዋጽኦ እያደረጉ ነው ብሏል።
#ዝዋይ በሚገኘው የካስትል ወይን ፋብሪካ አቅራቢያ ለሚኖሩ 500 ሰዎች የጤና መድን ሽፋን መግዛቱን የቢ ጂ አይ ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሄርቬ ሚልሃድ ተናግረዋል።
የጤና መድን ሽፋኑ የተገዛላቸው ሰዎች ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ናቸው ብለዋል።
በዚያው በዝዋይ አንድ የቅድመ መደበኛ #ትምህርት_ቤት አስገንብቶ ለአካባቢው ማህበረሰብ ማስረከቡን አክለዋል።
የአካባቢው ምህዳር ተጠብቆ እንዲቆይም ሠራተኞቹን እና ማህበረሰቡን በማስተባበር የተለያዩ ችግኞችን እየተከልን ነውም ብለዋል።
በዛሬው ዕለትም ዝዋይ በሚገኘው የካስቴል ወይን ፋብሪካ አቅራቢያ የኩባንያው ሠራተኞች እና የአካባቢው ነዋሪዎች 2000 ችግኞችን ተክለዋል።
ቢጂአይ ኢትዮጵያ የሜታ አቦ ፋብሪካን እና የተለያዩ ፋብሪካዎችን በመግዛት የማምረት አቅማቸውን እያሳደገ እንደሚገኝ ተነግሯል።
ንጋቱ ረጋሳ
Comentários