ሐምሌ 26፣2016 - በግለሰብ ሱቅ ውስጥ የተከማቸ ነዳጅ ለሰው ህይወት መጥፋት ምክንያት ሆኗል
- sheger1021fm
- Aug 2, 2024
- 1 min read
ትናንት በተከሰተ የእሳት አደጋ የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ በሁለት ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡
አደጋው የተከሰተው ትናንት ሀምሌ 25 ቀን 2016 ዓ.ም ምሽት በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ቡልቡላ ማርያም ማዞሪያ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ ነው፡፡
#የእሳት_አደጋዉ የተከሰተዉ በአንድ የመኪና ዕቃ መለዋወጫ ሱቅ ዉስጥ ሲሆን በሱቁ ተቀጥራ የምትሰራ የ20 ዓመት ወጣት በእሳት አደጋዉ ህይወቷ ወዲያው ማለፉ ተነግሯል።
በተጨማሪ ሁለት ሰዎች በጭስ የመታፈን ጉዳት እንደደረሰባቸው የአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መቆጣጠርና መከላከል ባለስልጣን ለሸገር ተናግሯል፡፡
የእሳት አደጋ ተስፋፍቶ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ መቆጣጠር እንደተቻለ በባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሞያ አቶ ንጋቱ ማሞ ነግረውናል፡፡
#ነዳጅ መከማቸት ያለበት በነዳጅ ማደያዎች መሆን ሲገባው በየግለሰብ ቤቶችና ሱቆች እየተከማቸ መሆኑ የእሳት አደጋ ሲከሰት የማባባስ አቅም ይኖራቸዋል የሚሉት ባለሙያው፣
በተከሰተው አደጋ ተከማችቶ የነበረው ነዳጅ ቃጠሎውን ያባባሰው በመሆኑ ተጎጂዋ እራሷን ማትረፍ እንዳትችል እንዳደረጋት ጠቁመዋል፡፡
ቃጠሎው የደረሰበት የመለዋወጫ ሱቅ ሙሉ በሙሉ በእሳቱ ወድሟል፤ መጠኑ ያልታወቀ ንብረት መውደሙንም ከላፊው ሰምተናል፡፡
ምንታምር ፀጋው
መሰገብገብ ለዚህ ይዳርጋል ገነናለገና አባት ለመሰብሰብ ተብሎ የሰው ሕይወት መጥፋት የለበት