top of page

ሐምሌ 26፣2016 - በኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች ያለው የፀጥታ ችግር ወደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሚጓጓዝ ዕርዳታ ላይ ዕክል እየፈጠረ ነው ተባለ

  • sheger1021fm
  • Aug 2, 2024
  • 1 min read

በኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች ያለው የፀጥታ ችግር ወደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሚጓጓዝ ዕርዳታ ላይ ዕክል እየፈጠረ ነው ተባለ።


የፌዴራል መንግስት ከአዲስ አበባ ለቤንሻኒጉል ጉሙዝ ክልል የሚልከው ዕርዳታ የኦሮሚያ እና አማራ ክልሎችን አቋርጦ ሲያልፍ በታጣቂዎች ይዘረፋል ተብሏል።


የቤንሻኒጉል ጉሙዝ ክልል በጎረቤት ሡዳን ያለውን ጦርነት በመሸሽ ወደ አካባቢው ለገቡ እንዲሁም በሌሎች ሠው ሰራሽ እና፤ ተፈጥሯዊ ምክንያቶች ድጋፍ ለሚፈልጉ ሰዎች የሚያከፋፍለው ዕርዳታ ከፌዴራል መንግስት እየተላከለት ቢሆንም፤ በአጎራባች ክልሎች ባለ የፀጥታ ችግር ምክንያት ማቅረቡ ፈተና እንደሆነበት ተናግሯል።


የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መሃመድ አብዱላዚዝ እንዳሉት፤ የተላከው ዕርዳታ አቋርጦ በሚያልፍባቸው የኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች የሚታየው የፀጥታ ችግር የማጓጓዙን ስራ ፈታኝ አድርጎታል።


ዕርዳታው ሁለቱም ክልሎች ላይ ሲደርስ በታጣቂዎች እንደሚያዝ የተናገሩት ኮሚሽነሩ፤ አንዳንዴም በድርድር፤ ሌላ ጊዜም ደግሞ በፀጥታ ሃይሎች ጣልቃ ገብነት ነው የሚለቀቀው ብለውናል።


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page